Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 3:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር መሆ​ኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደ​ር​ግህ ዘንድ እጀ​ም​ራ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “ከሙሴ ጋራ እንደ ነበርሁ ሁሉ፣ ከአንተም ጋራ መሆኔን ያውቁ ዘንድ፣ በእስራኤል ሁሉ ፊት አንተን ከፍ ከፍ ማድረጌን በዛሬዋ ዕለት እጀምራለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን እንዲያውቁ በዚህ ቀን አንተን በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ከፍ ከፍ ማድረግ እጀምራለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው፦ “ከሙሴ ጋር እንደ ነበርኩ ከአንተም ጋር የምሆን መሆኔን ያውቁ ዘንድ እኔ ዛሬ በእስራኤላውያን ሁሉ ፊት አንተን ከፍ፥ ከፍ ማድረግ እጀምራለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእስራኤል ሁሉ ዓይን ከፍ ከፍ አደርግህ ዘንድ እጀምራለሁ።

参见章节 复制




ኢያሱ 3:7
13 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገ​ነ​ነው፤ ከእ​ርሱ በፊ​ትም ለነ​በ​ሩት ነገ​ሥ​ታት ያል​ሆ​ነ​ውን የመ​ን​ግ​ሥት ክብር ሰጠው።


የዳ​ዊት ልጅ ሰሎ​ሞ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ በረታ፤ አም​ላ​ኩም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበረ፤ እጅ​ግም አከ​በ​ረው፤ አገ​ነ​ነ​ውም።


ሰው ምን​ድን ነው? ከፍ ከፍ ታደ​ር​ገው ዘንድ፥ ልቡ​ና​ው​ንም ትጐ​በ​ኘው ዘንድ፥


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ነገር ተና​ግሮ ዐይ​ኖ​ቹን ወደ ሰማይ አነ​ሣና እን​ዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደር​ሶ​አ​ልና ልጅህ ያከ​ብ​ርህ ዘንድ ልጅ​ህን አክ​ብ​ረው፤


በም​ንም እን​ደ​ማ​ላ​ፍር ተስፋ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁና እን​ደ​ታ​መ​ንሁ እንደ ወት​ሮው በልብ ደስታ በግ​ል​ጥ​ነት፥ አሁ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ክብር በሕ​ይ​ወ​ቴም ቢሆን፥ በሞ​ቴም ቢሆን በሰ​ው​ነቴ ይገ​ለ​ጣል።


በሁ​ሉም ለሙሴ እንደ ታዘ​ዝን እን​ዲሁ ለአ​ንተ ደግሞ እን​ታ​ዘ​ዛ​ለን፤ ብቻ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።


በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ የሚ​ቋ​ቋ​ምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበ​ርሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፥ ቸልም አል​ል​ህም።


እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።”


ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በሕ​ዝቡ ፊት ሂዱ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​መው በሕ​ዝቡ ፊት ሄዱ።


አሁ​ንም አንተ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ዳር ስት​ደ​ርሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ እዘዝ” አለው።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ሙሴ​ንም እንደ ፈሩ በዕ​ድ​ሜው ሁሉ ፈሩት።


跟着我们:

广告


广告