Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በደ​ረቅ መሬት ጸን​ተው ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በደ​ረቅ መሬት ተሻ​ገሩ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናትም፣ ሕዝቡ ሁሉ፣ ማለት እስራኤል በሙሉ ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል በደረቁ ምድር ላይ ቀጥ ብለው ቆመው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት በሚሻገሩ ጊዜ የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ሕዝቡ ሁሉ ዮርዳንስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሕዝቡ በደረቅ ምድር እየተራመዱ በሚሻገሩበት ጊዜ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ሕዝቡ ሁሉ ተሻግረው እስካበቁ ድረስ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል በደረቅ ምድር ላይ ቆመው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፥ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳንስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ።

参见章节 复制




ኢያሱ 3:17
14 交叉引用  

ኤል​ያ​ስም መጠ​ም​ጠ​ሚ​ያ​ውን ወስዶ ጠቀ​ለ​ለው፤ የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ውኃ መታ​በት፤ ውኃ​ውም ወዲ​ህና ወዲያ ተከ​ፈለ፤ ሁለ​ቱም በደ​ረቅ ተሻ​ገሩ። ወጥ​ተ​ውም በም​ድረ በዳው ቆሙ።


ምድር ፍሬ​ዋን ሰጠች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ይባ​ር​ከ​ናል፥ የም​ድ​ርም ዳርቻ ሁሉ ይፈ​ሩ​ታል።


ሙሴም በባ​ሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሌሊ​ቱን ሁሉ ጽኑ የአ​ዜብ ነፋስ አም​ጥቶ ባሕ​ሩን አስ​ወ​ገ​ደው፤ ባሕ​ሩ​ንም አደ​ረ​ቀው፤ ውኃ​ውም ተከ​ፈለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በባ​ሕሩ መካ​ከል በየ​ብስ ገቡ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በባ​ሕሩ ውስጥ በየ​ብስ ሄዱ፤ ውኃ​ውም በቀ​ኛ​ቸ​ውና በግ​ራ​ቸው እንደ ግድ​ግዳ ሆነ​ላ​ቸው።


ሞት ሰዎ​ችን ዋጠ፤ በረ​ታም፤ እንደ ገናም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፊት ሁሉ እን​ባን ያብ​ሳል፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ስድብ ከም​ድር ሁሉ ላይ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአፉ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ወደ ከነ​ዓን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤


በደ​ረቅ ምድር እንደ መሄድ የኤ​ር​ት​ራን ባሕር በእ​ም​ነት ተሻ​ገ​ሩ​አት፤ የግ​ብፅ ሰዎች ግን ሲሞ​ክሩ ሰጠሙ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሕዝቡ ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ እን​ዲ​ነ​ግር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጥ​ነው ተሻ​ገሩ።


ሕዝ​ቡም ሁሉ አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ ታቦተ ሕጉ ተሻ​ገ​ረች፤ እነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች በፊ​ታ​ቸው ተሻ​ገሩ።


ለል​ጆ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ትነ​ግ​ሯ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ፦ ‘እስ​ራ​ኤል ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን በደ​ረቅ ተሻ​ገረ፤’


በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል የካ​ህ​ናት እግር ከቆ​መ​በት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ቀላል ድን​ጋ​ዮ​ችን እን​ዲ​ያ​ነሡ እዘ​ዛ​ቸው፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ውሰ​ዱ​አ​ቸው፤ ከዚ​ያም ሌሊት በም​ታ​ድ​ሩ​በት ቦታ በየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ጠብ​ቋ​ቸው።”


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በባ​ሕር በኩል የነ​በ​ሩት የአ​ሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ በባ​ሕ​ሩም አጠ​ገብ የነ​በሩ የፊ​ኒ​ቃ​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የዮ​ር​ዳ​ኖ​ስን ውኃ እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ እን​ዳ​ደ​ረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባ​ቸው ቀለጠ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች የተ​ነሣ አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን ሳቱ።


跟着我们:

广告


广告