Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጮ​ሃ​ችሁ ጊዜ በእ​ና​ን​ተና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን መካ​ከል ደመ​ና​ንና ጭጋ​ግን አደ​ረ​ግሁ፤ ባሕ​ሩ​ንም መለ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤ አሰ​ጠ​ማ​ቸ​ውም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በግ​ብፅ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን አዩ፤ በም​ድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነርሱ ግን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እርሱም በእናንተና በግብጻውያን መካከል ጨለማ እንዲሆን አደረገ። ባሕሩን በላያቸው አመጣ፤ አሰጠማቸውም። በግብጻውያን ላይ ያደረግሁትንም ራሳችሁ በዐይናችሁ አያችሁ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ኖራችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ወደ ጌታም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፤ ዐይኖቻችሁም በግብጽ ያደረግሁትን አዩ፤ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እረዳቸው ዘንድ ወደ እኔ ጮኹ፤ እኔም በእነርሱና በግብጻውያን መካከል ጨለማ እንዲሆን አደረግሁ። ባሕሩም እንዲከነበልባቸው አድርጌ ግብጻውያንን አሰጠምሁ፤ በግብጻውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ በዐይኖቻችሁ አይታችኋል፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ለብዙ ጊዜ በበረሓ ኖራችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ወደ እግዚአብሔርም በጮኹ ጊዜ በእናንተና በግብፃውያን መካከል ጨለማ አደረገ፥ ባሕሩንም መለሰባቸው፥ አሰጠማቸውም፥ ዓይኖቻችሁም በግብፅ ያደረግሁትን አዩ፥ በምድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀመጣችሁ።

参见章节 复制




ኢያሱ 24:7
14 交叉引用  

ፈር​ዖ​ንም በቀ​ረበ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዐይ​ና​ቸ​ውን አነሡ፤ እነ​ሆም፥ ግብ​ፃ​ው​ያን ሲከ​ተ​ሉ​አ​ቸው አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅግ ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ።


በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሰፈ​ርና በእ​ስ​ራ​ኤል ሰፈር መካ​ከ​ልም ገባ፤ በዚ​ያም ጭጋ​ግና ጨለማ ነበረ፤ ሌሊ​ቱም አለፈ፤ ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ እርስ በእ​ር​ሳ​ቸው አል​ተ​ቃ​ረ​ቡም።


እስ​ራ​ኤ​ልም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ያደ​ረ​ጋ​ትን ታላ​ቂ​ቱን እጅ አዩ፤ ሕዝ​ቡም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈሩ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አመኑ፤ ባሪ​ያ​ው​ንም ሙሴን አከ​በሩ።


ቀድሞ እንደ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በ​ትም ዘመን መጠን በቃ​ዴስ ብዙ ቀን ተቀ​መ​ጣ​ችሁ።


የዛ​ሬ​ድ​ንም ፈፋ እስከ ተሻ​ገ​ር​ን​በት ድረስ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ማለ​ባ​ቸው ተዋ​ጊ​ዎች የሆኑ የዚ​ያች ትው​ልድ ሰዎች ከሰ​ፈሩ መካ​ከል እስከ ጠፉ ድረስ፥ ከቃ​ዴስ በርኔ የተ​ጓ​ዝ​ን​በት ዘመን ሠላሳ ስም​ንት ዓመት ሆነ።


ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሁሉ ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ በግ​ብፅ ምድር፥ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ሁሉ፥ በም​ድ​ሩም ሁሉ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በግ​ብፅ ለእ​ና​ንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈ​ተ​ናና በተ​አ​ም​ራት፥ በድ​ን​ቅና በሰ​ልፍ፥ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ማስ​ፈ​ራ​ራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሌላ ሕዝብ መካ​ከል ገብቶ ለእ​ርሱ ሕዝ​ብን ይወ​ስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥


አርባ ዘመን የተ​ቈ​ጣ​ቸ​ውስ እነ​ማን ነበሩ? የበ​ደሉ፥ ሬሳ​ቸ​ውም በም​ድረ በዳ የወ​ደ​ቀው አይ​ደ​ሉ​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ለእኛ ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር እን​ደ​ማ​ያ​ሳ​ያ​ቸው የማ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከግ​ብፅ የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያል​ሰሙ፥ እነ​ዚያ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አርባ ዓመት በመ​ድ​በራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር።


跟着我们:

广告


广告