Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 24:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በዚ​ያም ቀን ኢያሱ ከሕ​ዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በሴ​ሎም በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ድን​ኳን ፊት ሕግ​ንና ፍር​ድን ሰጣ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በዚያ ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ፤ የሚመሩበትንም ደንብና ሥርዐት እዚያው ሴኬም ሰጣቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በዚያም ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፥ በሴኬምም ሥርዓትና ፍርድ አደረገላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በዚያም ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን ገባ፤ በዚያም በሴኬም የሚመሩበትን ሕግና ሥርዓት ሰጣቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በዚያም ቀን ኢያሱ ከሕዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፥ በሴኬምም ሥርዓትና ፍርድ አደረገላቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 24:25
17 交叉引用  

በእ​ጃ​ቸው ያሉ​ት​ንም እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክት ሁሉ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም ያሉ​ትን ጉት​ቾች ለያ​ዕ​ቆብ ሰጡት፤ ያዕ​ቆ​ብም በሴ​ቄም አጠ​ገብ ካለ​ችው ዛፍ በታች ቀበ​ራ​ቸው። እስከ ዛሬም ድረስ አጠ​ፋ​ቸው።


ዮዳ​ሄም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በን​ጉሡ፥ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ ደግ​ሞም በን​ጉ​ሡና በሕ​ዝቡ መካ​ከል ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


በፍ​ጹም ልባ​ቸ​ውና በፍ​ጹም ነፍ​ሳ​ቸው የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይሹ ዘንድ ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤


በፍ​ጹ​ምም ልባ​ቸው ምለ​ዋ​ልና፥ በፍ​ጹ​ምም ሕሊ​ና​ቸው ፈል​ገ​ው​ታ​ልና፥ እር​ሱም ተገ​ኝ​ቶ​ላ​ቸ​ዋ​ልና ይሁዳ ሁሉ በመ​ሐ​ላው ደስ አላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዙ​ሪ​ያ​ቸው ዕረ​ፍ​ትን ሰጣ​ቸው።


ካህኑ ኢዮ​አ​ዳም በእ​ር​ሱና በሕ​ዝቡ ሁሉ፥ በን​ጉ​ሡም መካ​ከል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ቃል ኪዳን አደ​ረገ።


አሁ​ንም የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ከእኛ እን​ዲ​መ​ልስ ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ቃል ኪዳን አደ​ርግ ዘንድ በልቤ አስ​ቤ​አ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም ሁሉ የታ​መ​ነ​ውን ቃል ኪዳን አድ​ር​ገን እን​ጽ​ፋ​ለን፤ አለ​ቆ​ቻ​ች​ንም፥ ሌዋ​ው​ያ​ኖ​ቻ​ች​ንም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ያት​ሙ​በ​ታል።”


ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕን​ጨ​ትን አሳ​የው፤ በው​ኃ​ውም ላይ ጣለው፤ ውኃ​ውም ጣፈጠ። በዚ​ያም ሥር​ዐ​ት​ንና ፍር​ድን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፤ በዚ​ያም ፈተ​ና​ቸው።


ሙሴም ገባ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በአ​ንድ ድምፅ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃሎች ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኮ​ሬብ ካደ​ረ​ገው ቃል ኪዳን ሌላ በሞ​ዓብ ምድር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጋር ያደ​ር​ገው ዘንድ ሙሴን ያዘ​ዘው የቃል ኪዳኑ ቃሎች እነ​ዚህ ናቸው።


ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጠራ​ቸው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አቆ​ማ​ቸው።


ኢያ​ሱም ይህን ቃል ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መጽ​ሐፍ ጻፈው፤ ኢያ​ሱም ታላ​ቁን ድን​ጋይ ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በነ​በ​ረ​ችው በአ​ሆማ ዛፍ በታች አቆ​ማት።


跟着我们:

广告


广告