Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 22:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ካህኑ ፊን​ሐ​ስና የማ​ኅ​በሩ አለ​ቆች፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት የእ​ስ​ራ​ኤል መሳ​ፍ​ንት ሁሉ ፥ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ና​ገ​ሩ​ትን ቃል በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፤ ደስም አሰ​ኛ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ካህኑ ፊንሐስና የእስራኤላውያን የጐሣ መሪዎች የነበሩት የማኅበረ ሰቡ አለቆች የሮቤል፣ የጋድና የምናሴ ወገኖች ያሉትን በሰሙ ጊዜ ተደሰቱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል ነገድ አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃላት በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ካህኑ ፊንሐስና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሕዝቡ የላካቸው የምዕራብ ነገዶች የቤተሰብ አለቆች የሆኑት ታላላቅ ሰዎች፥ የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ በሚኖሩ የምናሴ ነገዶች ሕዝብ የተናገሩትን ሰምተው መልሱ አረካቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ካህኑ ፊንሐስና የማኅበሩ አለቆች፥ ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል አእላፋት አለቆች፥ የሮቤል ልጆችና የጋድ ልጆች የምናሴም ልጆች የተናገሩትን ቃል በሰሙ ጊዜ ነገሩ እጅግ ደስ አሰኛቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 22:30
11 交叉引用  

የከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም ሴቶች ልጆች በአ​ባቱ በይ​ስ​ሐቅ ፊት የተ​ጠሉ እንደ ሆኑ ዔሳው በአየ ጊዜ፥


ነገ​ሩም ንጉ​ሡ​ንና ጉባ​ኤ​ውን ሁሉ ደስ የሚ​ያ​ሰኝ ሆነ።


ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል።


ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ዝም አሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ሕ​ዛብ ደግሞ ለሕ​ይ​ወት የሚ​ሆን ንስ​ሓን ሰጣ​ቸው እንጃ” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ።


በድ​ን​ኳኑ ፊት ካለው ከአ​ም​ላ​ካ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሌላ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ለሰ​ላም መሥ​ዋ​ዕት፥ ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ትም የሚ​ሆን መሠ​ዊ​ያን የሠ​ራ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ በማ​መፅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዛሬ መከ​ተ​ልን ለመ​ተው በማ​ለት እንደ ሆነ ይህ ከእኛ ይራቅ።”


የካ​ህ​ኑም የአ​ል​ዓ​ዛር ልጅ ፊን​ሐስ ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች ለም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ፥ “ይህን መተ​ላ​ለፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን እን​ዳለ ዛሬ እና​ው​ቃ​ለን፤ አሁን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ አድ​ና​ች​ኋል” አላ​ቸው።


ነገ​ሩም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ደስ አሰኘ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በነ​ገ​ሩ​አ​ቸው ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገኑ፤ ከዚ​ያም ወዲያ የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትን ምድር ያጠፉ ዘንድ ለመ​ው​ጋት አን​ወ​ጣም ተባ​ባሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን አለ​ቆች ሔሬ​ብ​ንና ዜብን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋል እና​ንተ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን የሚ​መ​ስል እኔ ምን ማድ​ረግ እችል ኖር​አል?” አላ​ቸው። ከዚህ በኋላ ተዉት፤ ይህን ቃል በተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ መን​ፈ​ሳ​ቸው ዐረ​ፈች።


አን​ኩ​ስም ዳዊ​ትን ጠርቶ፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! አንተ በፊቴ ጻድ​ቅና ደግ ነህ፤ ከእ​ኔም ጋር በጭ​ፍ​ራው በኩል መው​ጣ​ት​ህና መግ​ባ​ትህ በፊቴ መል​ካም ነው፤ ወደ እኔ ከመ​ጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አን​ዳች ክፋት አላ​ገ​ኘ​ሁ​ብ​ህም፤ ነገር ግን በአ​ለ​ቆች ዘንድ አል​ተ​ወ​ደ​ድ​ህም።


跟着我们:

广告


广告