Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 21:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለቀ​ዓ​ትም ወገ​ኖች ልጆች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ለነ​በሩ ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ልጆች ከይ​ሁዳ ነገድ፥ ከስ​ም​ዖ​ንም ነገድ፥ ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ዘሮች በየጐሣቸው ወጣ፤ የካህኑ የአሮን ዝርያዎች ለሆኑት ሌዋውያን ከይሁዳ፣ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተመደቡላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ለቀዓትም ወገኖች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ወሰዱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የመጀመሪያው ዕጣ ለቀዓት ጐሣ ወጣ፤ ከሌዊ ነገድ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተከፋፈለ፤ እነዚህም ከተሞች የተወሰዱት ከይሁዳ፥ ከስምዖንና ከብንያም ነገዶች ይዞታዎች ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ለቀዓትም ወገኖች ዕጣ ወጣ፥ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ አሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ሆኑላቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 21:4
9 交叉引用  

በቀ​ኙም የሚ​ቆ​መው ወን​ድሙ አሳፍ ነበረ፤ አሳ​ፍም የበ​ራ​ክያ ልጅ፥ የሳ​ምዓ ልጅ፤


እነ​ዚ​ህም እንደ ወገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌ​ዊም የሕ​ይ​ወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።


እን​በ​ረ​ምም የአ​ባ​ቱን ወን​ድም ልጅ ዮካ​ብ​ድን አገባ፤ አሮ​ን​ንና ሙሴን፥ እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት፤ የእ​ን​በ​ረ​ምም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።


ለቀ​ዓ​ትም የእ​ን​በ​ረም ወገን፥ የይ​ስ​ዓር ወገን፥ የኬ​ብ​ሮ​ንም ወገን፥ የአ​ዛ​ሔ​ልም ወገን ነበሩ፤ የቀ​ዓት ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከር​ስ​ታ​ቸው እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ​አ​ቸው።


ለቀ​ሩ​ትም ለቀ​ዓት ልጆች ከኤ​ፍ​ሬም ነገድ፥ ከዳ​ንም ነገድ፥ ከም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ዐሥር ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።


የአ​ሮ​ንም ልጅ ሊቀ ካህ​ናቱ አል​ዓ​ዛር ሞተ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ለልጁ ለፊ​ን​ሐስ በተ​ሰ​ጠ​ችው በጊ​ብ​ዓት መሬት ቀበ​ሩት።


跟着我们:

广告


广告