Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በማ​ኅ​በሩ ፊት እስ​ኪ​ቆ​ምና እስ​ኪ​መ​ረ​መር ድረስ ባለ​ደሙ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው ሳያ​ውቅ ሰውን የገ​ደለ ወደ​ዚያ እን​ዲ​ማ​ፀን፥ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ፥ በመ​ካ​ካ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጥ መጻ​ተኛ የተ​መ​ረጡ ከተ​ሞች እነ​ዚህ ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሳያስበው በድንገት ሰው የገደለ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ወደ ተለዩት ከተሞች መሸሽ ይችላል፤ በማኅበሩ ፊት ከመቆሙ አስቀድሞም በደም ተበቃዩ መገደል የለበትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ለእስራኤል ሕዝብና በመካከላቸውም ለሚኖሩ መጻተኞች መማጸኛ ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ማንም ሰው በድንገተኛ አጋጣሚ ሰው ቢገድል፥ በሸንጎ ሳይፈረድበት እንዳይገደል ከእነዚያ ከተሞች ወደ አንዲቱ ሄዶ ሊበቀለው ከሚፈልገው ሰው እጅ ያመልጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በማኅበሩ ፊት እስኪቆም ድረስ በደም ተበቃዩ እጅ እንዳይሞት ሳያውቅ ሰውን የገደለ ወደዚያ እንዲሸሽ፥ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በመካከላቸውም ለሚቀመጥ መጻተኛ የተለዩ ከተሞች እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 20:9
5 交叉引用  

የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም ስድ​ስቱ ከተ​ሞች የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


ባለ​ማ​ወቅ ነፍስ የገ​ደለ ሁሉ ይሸ​ሽ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ዚህ ስድ​ስት ከተ​ሞች ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ለሚ​ቀ​መጡ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች መማ​ፀኛ ይሆ​ናሉ።


ከእ​ነ​ዚ​ህም ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ይማ​ፀ​ናል፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ቆሞ ለከ​ተ​ማ​ዪቱ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ነገ​ሩን ይና​ገ​ራል፤ እነ​ር​ሱም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ያገ​ቡ​ታል። የሚ​ቀ​መ​ጥ​በ​ትም ስፍራ ይሰ​ጡ​ታል።


በማ​ኅ​በሩ ፊት ለፍ​ርድ እስ​ኪ​ቆም ድረስ ፥ በዚ​ያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስ​ኪ​ሞት ድረስ በዚ​ያች ከተማ ይቀ​መጥ፤ ከዚ​ያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመ​ለ​ሳል፤ ወደ ከተ​ማ​ውም፥ ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣ​በ​ትም ከተማ ይገ​ባል።”


በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ማዶ ከኢ​ያ​ሪኮ ወደ ምሥ​ራቅ ከሮ​ቤል ነገድ በም​ድረ በዳው በደ​ል​ዳ​ላው ስፍራ ቦሶ​ርን፥ ከጋ​ድም ነገድ በገ​ለ​ዓድ ኤር​ሞ​ትን፥ ከም​ና​ሴም ነገድ በባ​ሳን ጎላ​ንን ለዩ።


跟着我们:

广告


广告