Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 17:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እነ​ር​ሱም ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛ​ርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለ​ቆ​ችም ቀር​በው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን መካ​ከል ርስት እን​ዲ​ሰ​ጠን በሙሴ እጅ አዘዘ” አሉ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ከአ​ባ​ታ​ቸው ወን​ድ​ሞች ጋር ርስት ሰጣ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፣ ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱና ወደ መሪዎቹ ቀርበው፣ “ከወንድሞቻችን ጋራ ርስት እንድንካፈል እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞታል” አሏቸው። ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት፣ ከአባታቸው ወንድሞች ጋራ ርስት ሰጣቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለቆችም ቀርበው እንዲህ አሉ፦ “ጌታ በወንድሞቻችን መካከል ርስት እንዲሰጠን ሙሴን አዘዘ፤” ጌታም እንዳዘዘ በአባታቸው ወንድሞች መካከል ርስት ሰጣቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነርሱም ወደ ካህኑ አልዓዛር፥ ወደ ነዌ ልጅ ኢያሱና ወደ መሪዎቹ ቀርበው “እንደ ወንዶች ዘመዶቻችን የርስት ድርሻ እንዲሰጠን እግዚአብሔር ሙሴን አዞታል” አሉአቸው። ስለዚህም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ለእነርሱ ከወንዶች ዘመዶቻቸው ጋር የርስት ድርሻ ተሰጣቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እነርሱም ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛርና ወደ ነዌ ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ አለቆችም ቀርበው፦ እግዚአብሔር በወንድሞቻችን መካከል ርስት እንዲሰጠን ሙሴን አዘዘ አሉ፥ እግዚአብሔርም እንዳዘዘ በአባታቸው ወንድሞች መካከል ርስት ሰጣቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 17:4
9 交叉引用  

ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ወገን ፥ የም​ናሴ ልጅ፥ የማ​ኪር ልጅ፥ የገ​ለ​አድ ልጅ፥ የኦ​ፌር ልጅ፥ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእ​ነ​ዚ​ህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ።


ወንድ ልጅስ ባይ​ኖ​ረው የአ​ባ​ታ​ችን ስም ከወ​ገኑ መካ​ከል ለምን ይጠ​ፋል?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው እን​ዲሁ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች አደ​ረጉ።


በዚ​ህም አይ​ሁ​ዳዊ፥ ወይም አረ​ማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አንድ ናች​ሁና።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በከ​ነ​ዓን ምድር የወ​ረ​ሱት ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ነገድ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አለ​ቆች ያወ​ረ​ሱ​አ​ቸው ርስት ይህ ነው።


ዕጣ​ቸ​ውም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ከአ​ለው ከገ​ለ​ዓ​ድና ከባ​ሳን ሀገር በቀር ለም​ናሴ ዐሥር ዕጣ ሆነ፤


የሌዊ ልጆች አለ​ቆች ወደ ካህኑ ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ አባ​ቶች ነገ​ዶች አለ​ቆች መጡ፤


跟着我们:

广告


广告