Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 14:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የዮ​ሴፍ ልጆች ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ሁለት ነገ​ዶች ነበሩ፤ ለሌ​ዋ​ው​ያ​ንም ከሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ከሚ​ሆን ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውና ከእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም በቀር በም​ድሩ ውስጥ ድርሻ አል​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ሆነው ነበርና፤ ለሌዋውያኑ ግን ከሚኖሩባቸው ከተሞች እንዲሁም ለበግ፣ ለፍየልና ለከብት መንጎቻቸው መሰማሪያ እንዲሆን ዐብሮ የተከለለላቸውን ምድር ብቻ እንጂ ሌላ አልሰጣቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን ማሰማርያ በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም በምድሪቱ ለመኖሪያቸው የሚሆኑ ከተሞችና ለከብቶቻቸው ማሰማሪያ የሚሆን መሬት በቀር የርስት ድርሻ አልተሰጣቸውም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፥ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን መሰምርያቸው በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።

参见章节 复制




ኢያሱ 14:4
13 交叉引用  

ዮሴ​ፍም የበ​ኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መከ​ራ​ዬን ሁሉ የአ​ባ​ቴ​ንም ቤት እን​ድ​ረሳ አደ​ረ​ገኝ፤”


የሁ​ለ​ተ​ኛ​ው​ንም ስም ኤፍ​ሬም ብሎ ጠራው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ከ​ራዬ ሀገር አብ​ዝ​ቶ​ኛ​ልና።”


ለዮ​ሴ​ፍም በግ​ብፅ ምድር ልጆች ተወ​ለ​ዱ​ለት፤ እነ​ር​ሱም የሄ​ል​ዮቱ ከተማ ካህን የጴ​ጤ​ፌራ ልጅ አስ​ኔት የወ​ለ​ደ​ች​ለት ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ናቸው። ሶር​ያ​ዊት ዕቅ​ብቱ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የም​ና​ሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ የም​ና​ሴም ወን​ድም የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ሱታ​ላና ጠኀን ናቸው። የሱ​ታላ ልጅም ኤዴን ነው።


ከዚ​ህም ነገር በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ “እነሆ፥ አባ​ታ​ችን ደከመ” ብለው ለዮ​ሴፍ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም ሁለ​ቱን ልጆ​ቹን ምና​ሴ​ንና ኤፍ​ሬ​ምን ይዞ ሄደ።


አሁ​ንም እኔ ወደ አንተ ከመ​ም​ጣቴ በፊት በግ​ብፅ ምድር የተ​ወ​ለ​ዱ​ልህ ሁለቱ ልጆ​ችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍ​ሬ​ምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤ​ልና እንደ ስም​ዖን ናቸው።


ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ የም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸው ልጆች ለአ​ንተ ይሁኑ፤ በር​ስ​ታ​ቸው በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ስም ይጠሩ።


ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፋሲካ ያደ​ርጉ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ዲ​መጡ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤ ደግ​ሞም ወደ ኤፍ​ሬ​ምና ወደ ምናሴ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ችን ጻፈ።


የአ​ሴር ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከኢ​ያ​ምን የኢ​ያ​ም​ና​ው​ያን ወገን፥ ከኢ​ያሱ የኢ​ያ​ሱ​ያ​ው​ያን ወገን፥ ከበ​ርያ የበ​ር​ያ​ው​ያን ወገን።


የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ምና​ሴና ኤፍ​ሬም ርስ​ታ​ቸ​ውን ወረሱ።


跟着我们:

广告


广告