Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ድን​በ​ራ​ቸ​ውም ኢያ​ዜ​ርና የገ​ለ​ዓድ ከተ​ሞች ሁሉ፥ የአ​ሞ​ንም ልጆች ምድር እኩ​ሌታ በራ​ባት ፊት እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አሮ​ዔር ድረስ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ድንበራቸው ኢያዜር፣ የገለዓድን ከተሞች በሙሉ በረባት አጠገብ እስካለው እስከ አሮዔር የሚደርሰውን የአሞናውያን አገር እኩሌታ፣

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ግዛታቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በረባት ፊት ለፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የእነርሱም ግዛት ያዕዜርንና በገለዓድ የሚገኙትን ከተሞች ሁሉ የዐሞንን ምድር እኩሌታ ጨምሮ ከራባ በስተምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ዓሮዔር ይደርሳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በረባት ፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥

参见章节 复制




ኢያሱ 13:25
21 交叉引用  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዓ​መቱ መጨ​ረሻ ነገ​ሥ​ታት ወደ ሰልፍ በሚ​ወ​ጡ​በት ጊዜ፥ ዳዊት ኢዮ​አ​ብን ከእ​ር​ሱም ጋር አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሁሉ ሰደደ። የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አጠፉ፤ አራ​ቦ​ት​ንም ከበቡ፤ ዳዊት ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቶ ነበር።


ኢዮ​አ​ብም የአ​ሞ​ንን ልጆች ከተማ ራባ​ትን ወጋ፤ የመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ው​ንም ከተማ ያዘ።


ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገሩ፤ በጋድ ሸለቆ መካ​ከል ባለ​ች​ውም በኢ​ያ​ዜር ከተማ ቀኝ በኩል በአ​ሮ​ዔር ላይ ሰፈሩ።


ከኬ​ብ​ሮ​ና​ው​ያ​ንም እንደ አባ​ቶች ቤቶች ትው​ል​ዶች የኬ​ብ​ሮ​ና​ው​ያን አለቃ ኤር​ያስ ነበረ። ዳዊት በነ​ገሠ በአ​ር​ባ​ኛው ዓመት ይፈ​ል​ጉ​አ​ቸው ነበረ፤ በእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል በገ​ለ​ዓድ ኢያ​ዜር ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎች ተገኙ፤


ሐሴ​ቦ​ንና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ፥ ኢያ​ዜ​ርና መሰ​ማ​ሪ​ያዋ ተሰጡ።


የሐ​ሴ​ቦን እር​ሻ​ዎ​ችና የሴ​ባማ ወይን ግን​ዶች አዝ​ነ​ዋል። የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች የሰ​ባ​በ​ሩ​አ​ቸው ቅር​ን​ጫ​ፎች እስከ ኢያ​ዜር ደር​ሰው ወደ ምድረ በዳ ወጥ​ተው ነበር፤ ቍጥ​ቋ​ጦ​ቹም ተዘ​ር​ግ​ተው ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረው ነበር።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ለመ​ንጋ ማሰ​ማ​ር​ያም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸ​ውም የለም።


አንቺ የሴ​ባማ ወይን ሆይ! የኢ​ያ​ዜ​ርን ልቅሶ ለአ​ንቺ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችሽ ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረ​ዋል፤ ወደ ኢያ​ዜ​ርም ባሕር ደር​ሰ​ዋል፤ ሳይ​በ​ስል በሰ​ብ​ል​ሽና በወ​ይ​ንሽ ላይ ጥፋት መጥ​ቶ​አል።


ሰይፍ ወደ አሞን ልጆች ሀገር፥ ወደ ራባት፥ ወደ ይሁ​ዳም፥ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም፥ በመ​ካ​ከ​ልዋ ይገባ ዘንድ መን​ገ​ድን አድ​ርግ።


በራባ ቅጥር ላይ እሳ​ትን አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ በጦ​ር​ነት ቀን በጩ​ኸት መሠ​ረ​ቶ​ች​ዋን ትበ​ላ​ለች፤ በፍ​ጻ​ሜ​ዋም ቀን ትና​ወ​ጣ​ለች።


ሙሴም ሰላ​ዮ​ቹን ወደ ኢያ​ዜር ላከ፤ እር​ስ​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋ​ንም ያዙ፤ በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አባ​ረሩ።


ሶፋ​ንን፥ ኢያ​ዜ​ርን፥


ለሎ​ጥም ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ ከአ​ሞን ልጆች ምድር ርስት አል​ሰ​ጥ​ህ​ምና በአ​ሞን ልጆች አቅ​ራ​ቢያ ስት​ደ​ርስ አት​ጣ​ላ​ቸው፤ አት​ው​ጋ​ቸ​ውም።’


ከራ​ፋ​ይ​ንም ወገን የባ​ሳን ንጉሥ ዐግ ብቻ​ውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አል​ጋው የብ​ረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአ​ሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝ​መቱ ዘጠኝ ክንድ ወር​ዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።


ገለ​ዓ​ድ​ንም፥ የጌ​ሴ​ሪ​ያ​ው​ያ​ን​ንና የመ​ከ​ጢ​ያ​ው​ያ​ንን ዳርቻ ሁሉ፥ የአ​ር​ሞ​ን​ዔ​ም​ንም ተራራ ሁሉ፥ ባሳ​ን​ንም ሁሉ፥ እስከ ሰልካ ድረስ፥


ሙሴም ለጋድ ነገድ ለጋ​ድም ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ሰጣ​ቸው።


ከሐ​ሴ​ቦን ጀምሮ እስከ አራ​ቦት መሴፋ፥ እስከ ቦጣ​ኒም ድረስ፥ ከማ​ኦን ጀምሮ እስከ ዴቦን ዳርቻ ድረስ፥


ሐሴ​ቦ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ኢያ​ዜ​ር​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ አራ​ቱን ከተ​ሞች ሰጡ።


ገለ​ዓድ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ተቀ​መጠ፤ ዳንም ለምን በመ​ር​ከብ ውስጥ ቀረ? አሴ​ርም በባ​ሕሩ ዳር ተቀ​መጠ፥ በወ​ን​ዞ​ቹም ዳርቻ ዐረፈ።


跟着我们:

广告


广告