Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 11:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያ​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ክፍ​ላ​ቸው በየ​ነ​ገ​ዳ​ቸው ርስት አድ​ርጎ ምድ​ሪ​ቱን ሰጣ​ቸው፤ ምድ​ሪ​ቱም ከጦ​ር​ነት ዐረ​ፈች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ምድሪቱን በሙሉ ያዘ፤ እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራኤላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ጌታም ለሙሴ እንደ ተናገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፤ ኢያሱም ለእስራኤል እንደየነገዳቸው ድርሻ ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፤ ምድሪቱም ከጦርነት ዐረፈች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኢያሱ ምድሩን ሁሉ በእጁ አደረገ፤ ለእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ድርሻ ርስት አድርጎ በመስጠት ለእስራኤላውያን በሙሉ አከፋፈለ። ስለዚህም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እግዚአብሔርም ለሙሴ እንደ ነገረው ሁሉ ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ ያዘ፥ ኢያሱም ለእስራኤል እንደ ክፍላቸውና እንደ ነገዳቸው ርስት አድርጎ ምድሪቱን ሰጣቸው፥ ምድሪቱም ከሰልፍ ዐረፈች።

参见章节 复制




ኢያሱ 11:23
20 交叉引用  

እነ​ር​ሱም ወረ​ሱ​አት፤ በከ​ነ​ዓን ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ት​ንም ሰዎች በፊ​ታ​ቸው አጠ​ፋ​ሃ​ቸው፤ የሚ​ወ​ድ​ዱ​ት​ንም ነገር ያደ​ር​ጉ​ባ​ቸው ዘንድ እነ​ር​ሱ​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ የም​ድ​ሩ​ንም አሕ​ዛብ በእ​ጃ​ቸው አሳ​ል​ፈህ ሰጠ​ሃ​ቸው።


የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች ከአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ጋር ተሰ​በ​ሰቡ፤ የም​ድር ኀይ​ለ​ኞች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ብለ​ዋ​ልና።


በዚህ ቀን የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ከፊ​ትህ አወ​ጣ​ለሁ።


ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ይዞታ ይሆ​ን​ለ​ታል፤ የሕ​ዝቤ አለ​ቆ​ችም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ምድ​ሪ​ቱን እንደ ነገ​ዳ​ቸው መጠን ይሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋል እንጂ ሕዝ​ቤን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ውም።”


በፊ​ትህ የሚ​ቆም የነዌ ልጅ ኢያሱ እርሱ ወደ​ዚያ ይገ​ባል፤ እር​ሱን አበ​ር​ታው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ምድ​ሪ​ቱን ያወ​ር​ሳ​ልና።


ስለ​ዚህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ በሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከሚ​ከ​ብ​ቡህ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሳ​ረ​ፈህ ጊዜ፥ የዐ​ማ​ሌ​ቅን ዝክረ ስሙን ከሰ​ማይ በታች አጥ​ፋው፤ ይህ​ንም አት​ርሳ።


ኢያ​ሱም ብዙ ዘመን ከእ​ነ​ዚሁ ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ኢያሱ በሊ​ባ​ኖስ ቆላ፥ በበ​ላ​ጋድ ባሕር፥ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሴይር በሚ​ደ​ርስ በኬ​ልኪ ተራራ የገ​ደ​ሉ​አ​ቸው የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥት እነ​ዚህ ናቸው። ኢያ​ሱም ያችን ምድር ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሰጣ​ቸው።


ኢያ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሴሎ ዕጣ አጣ​ጣ​ላ​ቸው።


አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አሳ​ር​ፎ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ተመ​ለሱ፤ ወደ ቤታ​ች​ሁና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ሂዱ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከብዙ ዘመን በኋላ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እስ​ራ​ኤ​ልን በዙ​ሪ​ያ​ቸው ካሉት ጠላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ካሳ​ረፈ በኋላ፥ ኢያሱ ሸመ​ገለ፤ ዘመ​ኑም ዐለፈ፤


跟着我们:

广告


广告