Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 10:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከአ​ዶ​ላም ወደ ኬብ​ሮን ወጡ፤ ወጉ​አ​ትም፤ ያዙ​አ​ትም፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 ከዚያም ኢያሱና ከርሱ ጋራ የነበሩት እስራኤላውያን በሙሉ ከዔግሎን ወደ ኬብሮን ወጡ፤ ወጓትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከዔግሎም ወደ ኬብሮን ወጡ፥ ወጉአትም፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ከዚህ በኋላ ኢያሱና ሠራዊቱ ከዔግሎን ወጥተው በኬብሮን ላይ አደጋ ጣሉባት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 ኢያሱም ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከኦዶላም ወደ ኬብሮን ወጡ፥ ወጉአትም፥ ያዙአትም፥

参见章节 复制




ኢያሱ 10:36
17 交叉引用  

አብ​ራ​ምም ድን​ኳ​ኑን ነቀለ፤ መጥ​ቶም በኬ​ብ​ሮን ባለው የመ​ምሬ ዛፍ ተቀ​መጠ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል የሳ​ኦ​ልን መን​ግ​ሥት ወደ እርሱ ይመ​ልሱ ዘንድ በኬ​ብ​ሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመ​ጡት የሠ​ራ​ዊቱ አለ​ቆች ቍጥር ይህ ነው።


ከእ​ር​ሱም ጋር ጽኑዕ ኀያል ጐል​ማሳ ሳዶቅ ነበረ፤ ከአ​ባ​ቱም ቤት ሃያ ሁለት አለ​ቆች ነበሩ።


ሶር​ዓን፥ ኤሎ​ንን፥ ኬብ​ሮ​ንን ሠራ።


ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብ​ሮ​ንም ደረሱ፤ በዚ​ያም የዔ​ናቅ ዘሮች አኪ​ማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብ​ሮ​ንም በግ​ብፅ ካለ​ችው ከጣ​ኔ​ዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመ​ታት ተሠ​ርታ ነበር።


ስለ​ዚ​ህም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ወደ ኬብ​ሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የር​ሙት ንጉ​ሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉ​ሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶ​ላም ንጉ​ሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ር​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ በዚ​ያም ቀን ያዙ​አት፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አት፤ በላ​ኪ​ስም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ፥ በእ​ር​ስዋ ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


እር​ስ​ዋ​ንም፥ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም፥ ከተ​ሞ​ች​ዋ​ንም ሁሉ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ፤ በአ​ዶ​ላም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም ፤ እር​ስ​ዋ​ንም፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።


አም​ስ​ቱም የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ነገ​ሥት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ የኬ​ብ​ሮን ንጉሥ፥ የየ​ር​ሙት ንጉሥ፥ የላ​ኪስ ንጉሥ፥ የአ​ዶ​ላም ንጉሥ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ጋር ተሰ​ብ​ስ​በው ወጡ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ጋር ሊጋ​ጠሙ ከበ​ቡ​አት።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ለዮ​ፎኒ ልጅ ለካ​ሌብ በይ​ሁዳ ልጆች መካ​ከል ድር​ሻ​ውን ሰጠው፤ ኢያ​ሱም የዔ​ናቅ ዋና ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን የአ​ር​ቦ​ቅን ከተማ ሰጠው። እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ናት።


ኤውማ፥ የአ​ር​ቦቅ ከተማ እር​ስ​ዋም ኬብ​ሮን ናት፥ ሶሬት፥ ዘጠኝ ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


ለካ​ህ​ኑም ለአ​ሮን ልጆች እነ​ዚ​ህን ሰጡ፤ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን ኬብ​ሮ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤ ሌም​ና​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥


ይሁ​ዳም በኬ​ብ​ሮን ወደ​ሚ​ኖሩ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ሄደ። የኬ​ብ​ሮ​ንም ሰዎች ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉት፤ የኬ​ብ​ሮ​ንም ስም አስ​ቀ​ድሞ ቂር​ያ​ታ​ር​ቦ​ቅ​ሴ​ፌር ነበረ። የኤ​ና​ቅ​ንም ትው​ልድ ሴሲ​ንና አኪ​ማ​ምን፥ ተለ​ሜ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።


ሙሴም እንደ ተና​ገረ ለካ​ሌብ ኬብ​ሮ​ንን ሰጡት፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ከተ​ሞ​ችን ወረሰ፤ ከዚ​ያም ሦስ​ቱን የዔ​ናቅ ልጆች አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告