Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 10:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ኢያ​ሱም፥ “በም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ሁሉ ላይ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋ​ልና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግጡ፤ ጽኑ፤ አይ​ዞ​አ​ችሁ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢያሱም፣ “አትፍሩ፤ አትደንግጡ፤ በርቱ፤ ጽኑ፤ እንግዲህ በምትወጓቸው ጠላቶች ሁሉ ላይ እግዚአብሔር እንደዚሁ ያደርጋልና” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢያሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ በምትወጉአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋልና አትፍሩ፥ አትደንግጡ፤ ጽኑ፥ አይዞአችሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ኢያሱም ለጦር መኰንኖቹ እንዲህ አለ፤ እግዚአብሔር ጦርነት በምትገጥሙአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ ልክ እንደዚህ ስለሚያደርግ አትፍሩ አይዞአችሁ፤ ቆራጥነትና ድፍረት ይኑራችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ኢያሱም፦ እግዚአብሔር በምትወጉአቸው በጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ እንዲሁ ያደርጋልና አትፍሩ፥ አትደንግጡ፥ ጽኑ፥ አይዞአችሁ አላቸው።

参见章节 复制




ኢያሱ 10:25
13 交叉引用  

ሰው ሁሉ ፈራ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥራ ተና​ገሩ፥ ሥራ​ው​ንም ዐወቁ።


ረድ​ኤ​ቱ​ንና ያሳ​ያ​ቸ​ውን ተአ​ም​ራ​ቱን ረሱ፥


ነገር ግን በወ​ደ​ደን በእ​ርሱ ሁሉን ድል እን​ነ​ሣ​ለን።


እር​ሱም እን​ዲህ ካለ ሞት አዳ​ነን፤ ያድ​ነ​ን​ማል፤ አሁ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ነን እር​ሱን እን​ታ​መ​ና​ለን።


እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በኀ​ይሉ ጽናት በርቱ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓይ​ንህ እያ​የች፥ ታላቅ መቅ​ሠ​ፍ​ትን፥ ምል​ክ​ት​ንም፥ ተአ​ም​ራ​ት​ንም፥ የጸ​ና​ች​ው​ንም እጅ፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ው​ንም ክንድ አድ​ርጎ እን​ዳ​ወ​ጣህ፤ እን​ዲሁ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንተ በም​ት​ፈ​ራ​ቸው በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ ያደ​ር​ጋል።


ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ የማ​ል​ሁ​ላ​ቸ​ውን ምድር ለዚህ ሕዝብ ታወ​ር​ሳ​ለ​ህና ጽና፥ በርታ።


እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው በፊ​ትህ የሚ​ተ​ርፍ የለም፤” አለው።


ዳዊ​ትም፥ “ከአ​ን​በ​ሳና ከድብ እጅ ያስ​ጣ​ለኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እጅ ያስ​ጥ​ለ​ኛል” አለ። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን” አለው።


跟着我们:

广告


广告