Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 10:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ኢያ​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በታ​ላቅ መም​ታት መም​ታ​ታ​ቸ​ውን በፈ​ጸሙ ጊዜ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ያመ​ለ​ጡት ወደ ተመ​ሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ ኢያሱና እስራኤላውያን እስከ መጨረሻው ደመሰሷቸው፤ የተረፉት ጥቂቶቹ ግን ወደ ተመሸጉት ከተሞቻቸው ለመድረስ ቻሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እስኪጠፉም ድረስ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች በጽኑ ውግያ ድል ማድረጋቸውን በፈጸሙ ጊዜ፥ ከእነርሱም ያመለጡት ወደ ተመሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ጥቂቶች ብቻ አምልጠው ወደ የከተሞቻቸው ምሽጎች ገብተው ከሞት ለመትረፍ ቢችሉም እንኳ ኢያሱና የእስራኤል ሰዎች ሁሉንም ዐረዱአቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እስኪጠፉም ድረስ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች በታላቅ መምታት መምታታቸውን በፈጸሙ ጊዜ፥ ከእነርሱም ያመለጡት ወደ ተመሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥

参见章节 复制




ኢያሱ 10:20
12 交叉引用  

ዳዊ​ትም አቢ​ሳን፥ “አሁን አቤ​ሴ​ሎም ከአ​ደ​ረ​ገ​ብን ይልቅ የከፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ግ​ብን የቢ​ኮሪ ልጅ ሳቡሄ ነው፤ እርሱ የተ​መ​ሸ​ጉ​ትን ከተ​ሞች አግ​ኝቶ ከዐ​ይ​ና​ችን እን​ዳ​ይ​ሰ​ወር፥ አንተ የጌ​ታ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ወስ​ደህ አሳ​ድ​ደው” አለው።


እነሆ፥ ክፉ ነገር አመ​ጣ​ብ​ሃ​ለሁ፤ እሳ​ትን ከኋ​ላህ አነ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ዐጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን ድረስ የአ​ክ​ዓ​ብን ዘር አጠ​ፋ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ያሉ​ት​ንም፥ የሌ​ሉ​ት​ንም እነ​ቅ​ላ​ለሁ፤


አብ​ያና ሕዝ​ቡም ታላቅ አመ​ታት መቱ​አ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ስት መቶ ሺህ የተ​መ​ረጡ ሰዎች ተገ​ድ​ለው ወደቁ።


በይ​ሁዳ ዘንድ ተና​ገሩ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ አው​ሩና፦ በሀ​ገ​ሪቱ ላይ መለ​ከት ንፉ በሉ፤ ጮኻ​ች​ሁም፦ ሁላ​ችሁ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ ወደ ተመ​ሸ​ጉ​ትም ከተ​ሞች እን​ግባ በሉ።


“ዝም ብለን ለምን እን​ቀ​መ​ጣ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ በደ​ልን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጥ​ፍ​ቶ​ና​ልና፥ የሐ​ሞ​ት​ንም ውኃ አጠ​ጥ​ቶ​ና​ልና ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ወደ ተመ​ሸጉ ከተ​ሞች እን​ግባ በዚ​ያም እን​ጥፋ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ምንም ነፍስ አታ​ድ​ንም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው፤ በገ​ባ​ዖ​ንም ታላቅ መም​ታት መታ​ቸው።


እና​ንተ ግን አት​ዘ​ግዩ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም እስከ መጨ​ረ​ሻው ተከ​ታ​ት​ላ​ችሁ ያዙ​አ​ቸው፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ገቡ ከል​ክ​ሉ​አ​ቸው፤” አለ።


ሕዝቡ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ መቄዳ በደ​ኅና ተመ​ለሱ፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ምላ​ሱን ማን​ቀ​ሳ​ቀስ የደ​ፈረ ማንም ሰው የለም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አገ​ል​ጋይ ሙሴ እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ ኢያሱ የእ​ነ​ዚ​ህን መን​ግ​ሥ​ታት ከተ​ሞች ሁሉ፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ያዘ፤ በሰ​ይ​ፍም መታ​ቸው፤ ፈጽ​ሞም አጠ​ፋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ መቱ​አ​ቸ​ውም፤ ወደ ታላ​ቂ​ቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴ​ሮ​ንም፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወዳ​ለው ወደ ሞሳሕ ሸለቆ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ማን​ንም ሳያ​ስ​ቀሩ መቱ​አ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተከ​ት​ለ​ዋ​ቸው በነ​በ​ረ​በት በተ​ራ​ራው ቍል​ቍ​ለ​ትና በም​ድረ በዳ የጋ​ይን ሰዎች መግ​ደ​ልን ከጨ​ረሱ፥ ሁሉ​ንም በጦር ወግ​ተው ከአ​ጠ​ፉ​አ​ቸው በኋላ ኢያሱ ወዲ​ያ​ውኑ ወደ ጋይ ተመ​ልሶ፥ በሰ​ይፍ አጠ​ፋት።


跟着我们:

广告


广告