Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢያሱ 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በሁ​ሉም ለሙሴ እንደ ታዘ​ዝን እን​ዲሁ ለአ​ንተ ደግሞ እን​ታ​ዘ​ዛ​ለን፤ ብቻ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ለሙሴ ሙሉ በሙሉ እንደ ታዘዝን ሁሉ፣ ለአንተም እንታዘዛለን፤ ብቻ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋራ እንደ ነበረ፣ አሁንም ከአንተ ጋራ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 በሁሉም ነገር ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን፤ ብቻ ጌታ አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ለሙሴ ሁልጊዜ ስንታዘዝለት እንደ ነበረ ሁሉ፥ ለአንተም እንታዘዛለን፤ እግዚአብሔር አምላክህ ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ፥ ከአንተም ጋር ይሁን!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በሁሉም ለሙሴ እንደ ታዘዝን እንዲሁ ለአንተ ደግሞ እንታዘዛለን፥ ብቻ አምላክህ እግዚአብሔር ከሙሴ ጋር እንደ ነበረ ከአንተ ጋር ይሁን።

参见章节 复制




ኢያሱ 1:17
19 交叉引用  

ያችም ሴት አለች፥ “መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን ነገር ለመ​ስ​ማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥ​ዋ​ዕ​ትና እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነውና የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ቃል እን​ደ​ዚሁ ነው፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጌ​ታዬ ከን​ጉሥ ጋር እንደ ነበረ እን​ዲሁ ከሰ​ሎ​ሞን ጋር ይሁን፤ ዙፋ​ኑ​ንም ከጌ​ታዬ ከን​ጉሡ ከዳ​ዊት ዙፋን የበ​ለጠ ያድ​ርግ።”


ዳዊ​ትም ልጁን ሰሎ​ሞ​ንን፥ “ጠን​ክር፤ ሰው ሁን፤ አይ​ዞህ፥ አድ​ር​ገ​ውም፤ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና አት​ፍራ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጥም፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ሆ​ነ​ውን ሥራ ሁሉ እስ​ክ​ት​ፈ​ጽም ድረስ እርሱ አይ​ተ​ው​ህም፤ አይ​ጥ​ል​ህ​ምም። እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአ​ደ​ባ​ባዩ፥ የቤተ መዛ​ግ​ብቱ፥ የሰ​ገ​ነቱ፥ የው​ስጡ ቤተ መዛ​ግ​ብት፥ የስ​ር​የት ቤቱና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ምሳሌ።


አቤቱ፥ በኀ​ይ​ልህ ንጉሥ ደስ ይለ​ዋል፤ በማ​ዳ​ን​ህም እጅግ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል።


ሕይ​ወ​ትን ለመ​ነህ፥ ሰጠ​ኸ​ውም፥ ለረ​ዥም ዘመን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ።


ፊትህ በተ​ቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድ​ር​ጋ​ቸው፤ አቤቱ፥ በቍ​ጣህ አው​ካ​ቸው፥ እሳ​ትም ትብ​ላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ ያለ​በ​ትን ሰው የነ​ዌን ልጅ ኢያ​ሱን ወስ​ደህ እጅ​ህን በላዩ ጫን​በት፤


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ እን​ዲ​ታ​ዘ​ዙት ከክ​ብ​ርህ ስጠው።


የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው! ሆሣዕና በአርያም!” እያሉ ይጮኹ ነበር።


ሙሴም እጆ​ቹን ስለ ጫነ​በት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ተሞላ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ታዘ​ዙ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።


እነ​ር​ሱም ለኢ​ያሱ እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ለት፥ “ያዘ​ዝ​ኸ​ንን ነገር ሁሉ እና​ደ​ር​ጋ​ለን ወደ​ም​ት​ል​ከ​ንም ስፍራ እን​ሄ​ዳ​ለን።


ለአ​ንተ የማ​ይ​ታ​ዘዝ፥ የም​ታ​ዝ​ዘ​ው​ንም ቃል የማ​ይ​ሰማ ሁሉ፥ እርሱ ይገ​ደል፤ አሁ​ንም ጽና፥ በርታ።”


በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ የሚ​ቋ​ቋ​ምህ የለም፤ ከሙሴ ጋር እንደ ነበ​ርሁ እን​ዲሁ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፥ ቸልም አል​ል​ህም።


እነሆ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በት ሁሉ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አት​ፍራ፥ አት​ደ​ን​ግ​ጥም።”


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢያ​ሱን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ሙሴ​ንም እንደ ፈሩ በዕ​ድ​ሜው ሁሉ ፈሩት።


ዳዊ​ትም፥ “ከአ​ን​በ​ሳና ከድብ እጅ ያስ​ጣ​ለኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ እጅ ያስ​ጥ​ለ​ኛል” አለ። ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን፥ “ሂድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር ይሁን” አለው።


አባ​ቴም በአ​ንተ ላይ ክፋት ማድ​ረግ ቢወ​ድድ፥ እኔም ባላ​ስ​ታ​ው​ቅህ፥ በሰ​ላ​ምም ትሄድ ዘንድ ባላ​ሰ​ና​ብ​ትህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዮ​ና​ታን ይህን ያድ​ርግ፤ ይህ​ንም ይጨ​ምር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ባቴ ጋር እንደ ነበረ ከአ​ንተ ጋር ይሁን።


跟着我们:

广告


广告