1 ዮናስም ፈጽሞ አዘነ፤ ተከዘም።
1 ዮናስ ግን ፈጽሞ አልተደሰተም፤ ስለዚህም ተቈጣ።
1 ይህም ዮናስን ከቶ ደስ አላሰኘውም፥ ክፉኛም አበሳጨው።
1 ዮናስ በዚህ ነገር ስላልተደሰተ ተበሳጨ፤
እግዚአብሔርም ዮናስን፥ “ፈጽመህ ታዝናለህን?” አለው።
እግዚአብሔርም ዮናስን፥ “በውኑ ስለዚች ቅል ታዝናለህን?” አለው። እርሱም፥ “እስክሞት ድረስ እጅግ አዝኛለሁ” አለ።
ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዐይንህ ምቀኛ ናትን?
ተቈጥቶም ‘አልገባም’ አለ፤ አባቱም ወጥቶ ማለደው።
የጠራው ፈሪሳዊም ባየ ጊዜ በልቡ ዐሰበ፤ እንዲህም አለ፥ “ይህስ ነቢይ ቢሆን ኖሮ ይህቺ የምትዳስሰው ሴት ማን እንደ ሆነች፥ እንዴትስ እንደ ነበረች ባላወቀም ነበርን? ኀጢአተኛ ናትና።”
ጳውሎስና በርናባስም ደፍረው እንዲህ ብለው ተናገሩአቸው፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ለእናንተ አስቀድሞ ልንነግራችሁ ይገባል፤ እንቢ ብትሉና ራሳችሁን ለዘለዓለም ሕይወት የተዘጋጀ ባታደርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕዛብ እንመለሳለን።