Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮናስ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እር​ሱም፥ “ይህ ታላቅ ማዕ​በል በእኔ ምክ​ን​ያት እንደ አገ​ኛ​ችሁ ዐው​ቃ​ለ​ሁና አን​ሥ​ታ​ችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕ​ሩም ጽጥ ይል​ላ​ች​ኋል” አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እርሱም፣ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንደ መጣባችሁ ዐውቃለሁ፤ አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ባሕሩም ጸጥ ይላል” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እርሱም፦ “ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት እንደመጣባችሁ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፥ ባሕሩም ጸጥ ይልላችኋል” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ዮናስም “ይህ ማዕበል በእናንተ ላይ የመጣው በእኔ በደል ምክንያት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ እኔን አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ፤ ማዕበሉም ጸጥ ይልላችኋል” አላቸው።

参见章节 复制




ዮናስ 1:12
10 交叉引用  

ዳዊ​ትም ሕዝ​ቡን የሚ​መ​ታ​ውን መል​አክ ባየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “እነሆ፥ እኔ በድ​ያ​ለሁ፤ ክፉም ሥራ እኔ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እነ​ዚህ በጎች ግን ምን አደ​ረጉ? እጅህ በእ​ኔና በአ​ባቴ ቤት ላይ ትሆን ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ረው።


ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ሕዝቡ ይቈ​ጠር ዘንድ ያዘ​ዝሁ እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? የበ​ደ​ል​ሁና ክፉ የሠ​ራሁ እኔ ነኝ፤ እነ​ዚህ በጎች ግን ምን አድ​ር​ገ​ዋል? አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እጅህ በእ​ኔና በአ​ባቴ ቤት ላይ ትሁን፤ ነገር ግን አቤቱ በሕ​ዝ​ብህ ላይ ለጥ​ፋት አት​ሁን” አለው።


እንደ አንተ ያለ​ውን ሰው ክፋ​ትህ ይጎ​ዳ​ዋል፤ ለሰ​ውም ልጅ ጽድ​ቅህ ይጠ​ቅ​መ​ዋል።


ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎች ይልቅ ጥበብ ትሻ​ላ​ለች፤ አንድ ኀጢ​አ​ተኛ ግን ብዙ መል​ካ​ምን ያጠ​ፋል።


ባሕሩ ይታ​ወክ ነበ​ርና፥ ታላቅ ማዕ​በ​ልም ተነ​ሥቶ ነበ​ርና፥ “ባሕሩ ጸጥ ይል​ልን ዘንድ እን​ግ​ዲህ ምን እና​ድ​ር​ግህ?” አሉት።


ሰዎቹ ግን ወደ ምድሩ ሊመ​ለሱ አጥ​ብ​ቀው ቀዘፉ፤ ዳሩ ግን ባሕሩ እጅግ አብ​ዝቶ ይና​ወ​ጥ​ባ​ቸው ነበ​ርና አል​ቻ​ሉም።


ምንም አት​መ​ክ​ሩም፤ ሕዝቡ ሁሉ ከሚ​ጠፋ ስለ ሕዝቡ አንድ ሰው ቢሞት ይሻ​ለ​ናል።”


እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፦ ‘ጳው​ሎስ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቄ​ሣር ፊት ልት​ቆም ይገ​ባ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም ጋር የሚ​ሄ​ዱ​ትን ሁሉ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሰጥ​ቶ​ሃል።’


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት መቆም አይ​ች​ሉም፤ የተ​ረ​ገሙ ስለ​ሆኑ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ፊት ይሸ​ሻሉ፤ እርም የሆ​ነ​ው​ንም ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ካላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከዚህ በኋላ ከእ​ና​ንተ ጋር አል​ሆ​ንም።


跟着我们:

广告


广告