Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 8:52 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 አይ​ሁ​ድም እን​ዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እን​ዳ​ለ​ብህ ዐወ​ቅን፤ አብ​ር​ሃም ስንኳ ሞቶ​አል፤ ነቢ​ያ​ትም ሞተ​ዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም ትላ​ለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 አይሁድም እንዲህ አሉት፤ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ማንም ቃልህን ቢጠብቅ ሞትን ፈጽሞ እንደማይቀምስ ትናገራለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 አይሁድ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም እንኳን ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም፤’ ትላለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 አይሁድ እንዲህ አሉት፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም እንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ አይሞትም’ ትላለህ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

52 አይሁድ፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን አወቅን። አብርሃም ስንኳ ሞተ ነቢያትም አንተም፦ ‘ቃሌን የሚጠብቅ ቢኖር ለዘላለም ሞትን አይቀምስም’ ትላለህ።

参见章节 复制




ዮሐንስ 8:52
14 交叉引用  

ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘ጋኔን አለበት’ አሉት።


አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አለው፥ “የሚ​ወ​ደኝ ቃሌን ይጠ​ብ​ቃል፤ አባ​ቴም ይወ​ደ​ዋል፤ ወደ እር​ሱም መጥ​ተን በእ​ርሱ ዘንድ ማደ​ሪያ እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


እኔ፦ ከጌ​ታው የሚ​በ​ልጥ አገ​ል​ጋይ የለም ያል​ኋ​ች​ሁን ቃሌን ዐስቡ፤ እኔን ካሳ​ደዱ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ቃሌን ጠብ​ቀው ቢሆ​ንስ ቃላ​ች​ሁ​ንም በጠ​በቁ ነበር።


“ከዓ​ለም ለይ​ተህ ለሰ​ጠ​ኸኝ ሰዎች ስም​ህን ገለ​ጥሁ፤ ያንተ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለእኔ ሰጥ​ተ​ኸ​ኛል፤ ቃል​ህ​ንም ጠበቁ።


ሕዝ​ቡም፥ “ጋኔን አለ​ብ​ህን? ማን ሊገ​ድ​ልህ ይሻል?” ብለው መለ​ሱ​ለት።


አይ​ሁ​ድም፥ “እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አት​ች​ሉም የሚ​ለን እርሱ ራሱን ይገ​ድል ይሆን? እንጃ!” አሉ።


አይ​ሁ​ድም፥ “አንተ ሳም​ራዊ እንደ ሆንህ፥ ጋኔ​ንም እንደ አለ​ብህ መና​ገ​ራ​ችን በሚ​ገባ አይ​ደ​ለ​ምን?” ብለው ጠየ​ቁት።


እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ቃሌን የሚ​ጠ​ብቅ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሞትን አይ​ቀ​ም​ስም።”


እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ እኔ ግን ኣው​ቀ​ዋ​ለሁ፤ አላ​ው​ቀ​ውም ብልም እንደ እና​ንተ ሐሰ​ተኛ እሆ​ና​ለሁ፤ እኔ አው​ቀ​ዋ​ለሁ ቃሉ​ንም እጠ​ብ​ቃ​ለሁ።


ዕውር የነ​በ​ረ​ው​ንም ሰው ዳግ​መኛ ጠር​ተው፥ “ሂድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና አቅ​ርብ፤ ይህ ሰው ኀጢ​ኣ​ተኛ እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን” አሉት።


እነ​ዚህ ሁሉ አም​ነው ሞቱ፤ ተስ​ፋ​ቸ​ው​ንም አላ​ገ​ኙም፤ ነገር ግን ከሩቅ አይ​ተው እጅ ነሱ​ኣት፤ በም​ድ​ሪ​ቱም ላይ እነ​ርሱ እን​ግ​ዶ​ችና መጻ​ተ​ኞች እንደ ሆኑ ዐወቁ።


ነገር ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ስለ ሰው ሁሉ ሞትን ይቀ​ምስ ዘንድ ከመ​ላ​እ​ክት ይልቅ በጥ​ቂት አንሶ የነ​በ​ረ​ውን ኢየ​ሱ​ስን ከሞት መከራ የተ​ነሣ የክ​ብ​ርና የም​ስ​ጋ​ናን ዘውድ ጭኖ እና​የ​ዋ​ለን።


跟着我们:

广告


广告