Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 8:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውና የም​ፈ​ር​ደው ብዙ አለኝ፤ የላ​ከ​ኝም እው​ነ​ተኛ ነው፤ እኔ በእ​ርሱ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ለዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በእናንተ ላይ ብዙ የምናገረውና ብዙ የምፈርደው ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ ታማኝ ነው፤ ከርሱም የሰማሁትን ለዓለም እናገራለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ፤” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ ነገር አለኝ፤ ይሁን እንጂ የላከኝ እውነተኛ ነው፤ እኔም ለዓለም የምናገረው ከእርሱ የሰማሁትን ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለ እናንተ የምናገረው የምፈርደውም ብዙ ነገር አለኝ፤ ዳሩ ግን የላከኝ እውነተኛ ነው እኔም ከእርሱ የሰማሁትን ይህን ለዓለም እናገራለሁ” አላቸው።

参见章节 复制




ዮሐንስ 8:26
17 交叉引用  

እን​ግ​ዲህ ወዲህ ባሮች አል​ላ​ች​ሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና፤ እና​ን​ተን ግን ወዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ባቴ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ሁሉ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


“የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ብዙ ነገር ነበ​ረኝ፤ ነገር ግን አሁን ልት​ሸ​ከ​ሙት አት​ች​ሉም።


የሰ​ጠ​ኽ​ኝን ቃል ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ተቀ​ብ​ለው ከአ​ንተ እንደ ወጣሁ በእ​ው​ነት ዐወቁ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ አመኑ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።


እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ የም​ና​ው​ቀ​ውን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ያየ​ነ​ው​ንም እን​መ​ሰ​ክ​ራ​ለን፤ ነገር ግን ምስ​ክ​ር​ነ​ታ​ች​ንን አት​ቀ​በ​ሉ​ንም።


ስለ​ዚ​ህም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ትም​ህ​ርቴ የላ​ከኝ ናት እንጂ የእኔ አይ​ደ​ለ​ችም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ምር ቃሉን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “እኔን ታው​ቁ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ራሴ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት የላ​ከኝ እው​ነ​ተኛ አለ።


እነ​ር​ሱም፥ “አንተ ማነህ?” አሉት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “በመ​ጀ​መ​ሪያ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ።


ነገር ግን ስለ አብ እንደ ነገ​ራ​ቸው አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።


አሁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን እው​ነት የም​ነ​ግ​ራ​ች​ሁን ሰው ልት​ገ​ድ​ሉኝ ትሻ​ላ​ችሁ፤ አብ​ር​ሃ​ምስ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ገም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም የሚ​ነ​ገ​ረው ቃላ​ችን እው​ነ​ትና ሐሰት አል​ተ​ቀ​ላ​ቀ​ለ​በ​ትም።


跟着我们:

广告


广告