Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 7:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 “ክር​ስ​ቶስ ነው” ያሉም አሉ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ቹም እን​ዲህ አሉ፥ “በውኑ ክር​ስ​ቶስ ከገ​ሊላ ይወ​ጣ​ልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ሌሎችም፣ “እርሱ ክርስቶስ ነው” አሉ። ሌሎች ደግሞ እንዲህ አሉ፤ “ክርስቶስ ከገሊላ እንዴት ሊመጣ ይችላል?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ሌሎች “ይህ ክርስቶስ ነው፤” አሉ፤ ሌሎች ግን “ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን? አሉ

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ሌሎች “ይህ መሲሕ ነው” አሉ። ሌሎቹ ግን “መሲሕ የሚመጣው ከገሊላ ነውን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ሌሎች፦ “ይህ ክርስቶስ ነው” አሉ፤ ሌሎች ግን፦ “ክርስቶስ በእውኑ ከገሊላ ይመጣልን?

参见章节 复制




ዮሐንስ 7:41
11 交叉引用  

ከዮ​ሐ​ንስ ዘንድ ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከተ​ከ​ተ​ሉት ከሁ​ለ​ቱም አንዱ የስ​ም​ዖን ጴጥ​ሮስ ወን​ድም እን​ድ​ር​ያስ ነበር።


ፊል​ጶ​ስም ናት​ና​ኤ​ልን አገ​ኘ​ውና፥ “ሙሴ በኦ​ሪት፥ ነቢ​ያ​ትም ስለ እርሱ የጻ​ፉ​ለ​ትን የዮ​ሴ​ፍን ልጅ የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን አገ​ኘ​ነው” አለው።


ናት​ና​ኤ​ልም፥ “በየት ታው​ቀ​ኛ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ገና ፊል​ጶስ ሳይ​ጠ​ራህ በበ​ለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አይ​ች​ሃ​ለሁ” አለው።


ሴቲ​ቱም፥ “ክር​ስ​ቶስ የሚ​ሉት መሲሕ እን​ደ​ሚ​መጣ እና​ው​ቃ​ለን፤ እር​ሱም በሚ​መጣ ጊዜ ሁሉን ይነ​ግ​ረ​ናል” አለ​ችው።


“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ የነ​ገ​ረ​ኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ይሆን?”


ሴቲ​ቱ​ንም፥ “እኛ ራሳ​ችን ይህ በእ​ው​ነት የዓ​ለም መድ​ኀ​ኒት ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ሰም​ተ​ንና ተረ​ድ​ተን ነው እንጂ በአ​ንቺ ቃል ያመ​ን​በት አይ​ደ​ለም” አሏት።


እኛስ የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ አንተ እንደ ሆንህ አም​ነ​ናል፤ አው​ቀ​ና​ልም።”


ነገር ግን ይህን ከየት እንደ ሆነ እና​ው​ቃ​ለን፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜስ ከወ​ዴት እንደ ሆነ ማንም አያ​ው​ቅም”።


ከሕ​ዝ​ቡም ብዙ​ዎች አመ​ኑ​በ​ትና፥ “በውኑ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ጊዜ ይህ ሰው ካደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት የሚ​በ​ልጥ ያደ​ር​ጋ​ልን?” አሉ።


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “አን​ተም ደግሞ ከገ​ሊላ ነህን? ከገ​ሊላ ነቢይ እን​ደ​ማ​ይ​ነሣ መር​ም​ርና እይ” አሉት።


跟着我们:

广告


广告