Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 5:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ያሳ​ድ​ዱ​ትና ሊገ​ድ​ሉ​ትም ይሹ ነበር፤ በሰ​ን​በት እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበ​ርና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 አይሁድም፣ በሰንበት ቀን እነዚህን ድርጊቶች በመፈጸሙ፣ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለዚህም አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር፤ በሰንበት ይህን አድርጎ ነበርና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይህን ነገር በሰንበት ስላደረገ የአይሁድ ባለሥልጣኖች ኢየሱስን ያሳድዱት ጀመር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር።

参见章节 复制




ዮሐንስ 5:16
15 交叉引用  

ከዚያም በኋላ ሰውየውን “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። ዘረጋትም፤ እንደ ሁለተኛይቱም ደህና ሆነች።


ፈሪሳውያንም ወጥተው ወዲያው እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ከሄሮድስ ወገን ጋር ተማከሩበት።


እነ​ርሱ ግን፥ እጅግ ተቈጡ፤ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ምን እን​ድ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​በት እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ከሩ።


አይ​ሁድ፥ “አንተ ማን ነህ?” ብለው ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ካህ​ና​ት​ንና ሌዋ​ው​ያ​ንን ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በላኩ ጊዜ የዮ​ሐ​ንስ ምስ​ክ​ር​ነት ይህ ነው።


ዳግ​መ​ኛም ሊይ​ዙት ፈለጉ፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም አመ​ለጠ።


እኔ፦ ከጌ​ታው የሚ​በ​ልጥ አገ​ል​ጋይ የለም ያል​ኋ​ች​ሁን ቃሌን ዐስቡ፤ እኔን ካሳ​ደዱ እና​ን​ተ​ንም ያሳ​ድ​ዱ​አ​ች​ኋል፤ ቃሌን ጠብ​ቀው ቢሆ​ንስ ቃላ​ች​ሁ​ንም በጠ​በቁ ነበር።


አይ​ሁ​ድም የዳ​ነ​ውን ሰው፥ “ዛሬ ሰን​በት ነው፤ አል​ጋ​ህን ልት​ሸ​ከም አይ​ገ​ባ​ህም” አሉት።


ያ የተ​ፈ​ወ​ሰው ግን ያዳ​ነው ማን እንደ ሆነ አላ​ወ​ቀም፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በዚያ ቦታ በነ​በ​ሩት ብዙ ሰዎች መካ​ከል ተሰ​ውሮ ነበ​ርና።


ያም ሰው ሄዶ ያዳ​ነው ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ ሆነ ለአ​ይ​ሁድ ነገ​ራ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠ​ራል፤ እኔም እሠ​ራ​ለሁ” አላ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት በጣም ይፈ​ልጉ ነበር፤ “ሰን​በ​ትን የሚ​ሽር ነው” በማ​ለት ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን “አባቴ ነው ይላል፤ ራሱ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ያስ​ተ​ካ​ክ​ላል” በማ​ለት ነው እንጂ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ አላ​ቸው፥ “አንድ ሥራ ሠራሁ፤ ሁላ​ች​ሁም አደ​ነ​ቃ​ችሁ።


ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሰዎ​ችም እን​ዲህ የሚሉ ነበሩ፥ “ይህ አይ​ሁድ ሊገ​ድ​ሉት የሚ​ሹት አይ​ደ​ለ​ምን?


跟着我们:

广告


广告