Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ያቺ ሴትም እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ መቅጃ እንኳ የለ​ህም፤ ጕድ​ጓ​ዱም ጥልቅ ነው፤ እን​ግ​ዲህ የሕ​ይ​ወት ውኃ ከወ​ዴት ታገ​ኛ​ለህ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ፣ መቅጃ የለህም፤ ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ ታዲያ ይህን የሕይወት ውሃ ከየት ታገኛለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሴቲቱ “ጌታ ሆይ! መቅጃ የለህም፤ ጉድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውሃ ከወዴት ታገኛለህ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰች፤ “ጌታ ሆይ! አንተ መቅጃ የለህም፤ ጒድጓዱም ጥልቅ ነው፤ ታዲያ፥ የሕይወት ውሃ ከየት ታገኛለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሴቲቱ፦ ጌታ ሆይ፥ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ?

参见章节 复制




ዮሐንስ 4:11
10 交叉引用  

ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገ​ሮ​ችን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የሕ​ይ​ወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተ​ው​ኛል፥ የተ​ነ​ደ​ሉ​ትን ውኃ​ው​ንም ይይዙ ዘንድ የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ጕድ​ጓ​ዶች ለራ​ሳ​ቸው ቈፍ​ረ​ዋል።


ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም፥ “ሰው ከሸ​መ​ገለ በኋላ ዳግ​መኛ መወ​ለድ እን​ደ​ምን ይች​ላል? ዳግ​መኛ ይወ​ለድ ዘንድ ወደ እናቱ ማኅ​ፀን ተመ​ልሶ መግ​ባት ይች​ላ​ልን?” አለው።


እኔ ከም​ሰ​ጠው ውኃ የሚ​ጠጣ ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ጠ​ማም፤ እኔ የም​ሰ​ጠው ውኃ በው​ስጡ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የሚ​ፈ​ልቅ የውኃ ምንጭ ይሆ​ን​ለ​ታል እንጂ።”


በኋ​ለ​ኛ​ዪቱ በታ​ላ​ቅዋ የበ​ዓል ቀንም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ቆመና ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “የተ​ጠማ ወደ እኔ ይም​ጣና ይጠጣ።


ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አቤቱ፥ ከቶ አይ​ሆ​ንም፤ ርኩስ፥ የሚ​ያ​ጸ​ይ​ፍም ከቶ በልች አላ​ው​ቅም” አለው።


ለሥ​ጋዊ ሰው ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነገር ሞኝ​ነት ይመ​ስ​ለ​ዋ​ልና፥ አይ​ቀ​በ​ለ​ውም፤ በመ​ን​ፈ​ስም የሚ​መ​ረ​መር ስለ​ሆነ ሊያ​ውቅ አይ​ች​ልም።


አለኝም “ተፈጽሞአል፤ አልፋና ዖሜጋ፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። ለተጠማ ከሕይወት ውሃ ምንጭ እንዲያው እኔ እሰጣለሁ።


በአደባባይዋም መካከል ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውሃ ወንዝ አሳየኝ።


መንፈሱና ሙሽራይቱም “ና!” ይላሉ። የሚሰማም “ና!” ይበል። የተጠማም ይምጣ፤ የወደደም የሕይወትን ውሃ እንዲያው ይውሰድ።


በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”


跟着我们:

广告


广告