Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 21:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ የሠ​ራ​ቸው ሌሎች ብዙ ሥራ​ዎች አሉ፤ ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ቢጻፍ ግን የተ​ጻ​ፉ​ትን መጻ​ሕ​ፍት ዓለም ስን​ኳን ባል​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበር። ከዐ​ሥራ ሁለቱ ሐዋ​ር​ያት አንዱ የዘ​ብ​ዴ​ዎስ ልጅ ሐዋ​ር​ያው ዮሐ​ንስ ጌታ​ችን በሥጋ ወደ ሰማይ ባረገ በሠ​ላሳ ዓመት፥ ቄሳር ኔሮን በነ​ገሠ በሰ​ባት ዓመት በዮ​ና​ና​ው​ያን ቋንቋ ለኤ​ፌ​ሶን ሰዎች የጻ​ፈ​ፍው ወን​ጌል ተፈ​ጸመ። ምስ​ጋና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁን። አሜን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎችም ብዙ ነገሮች አሉ፤ ሁሉም ነገር ቢጻፍ፣ ለተጻፉት መጻሕፍት ሁሉ ዓለም በቂ ቦታ የሚኖረው አይመስለኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢየሱስም ያደረገው ሌላ ብዙ ነገር አለ፤ ሁሉም አንድ በአንድ ቢጻፍ፥ እንደሚመስለኝ፥ ዓለም እራሱ የሚጻፉትን መጻሕፍት ለመያዝ ቦታ አይበቃውም ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ኢየሱስ ያደረጋቸው ሌሎች ብዙ ነገሮች ደግሞ አሉ። እኔ እንደሚመስለኝ እርሱ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ ቢጻፉ ኖሮ የሚጻፉትን መጻሕፍት ዓለም ራሱ መሸከም ባልቻለም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ኢየሱስም ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።

参见章节 复制




ዮሐንስ 21:25
12 交叉引用  

እነሆ ይህ የመ​ን​ገዱ ክፍል ነው፤ የቀ​ሩ​ት​ንም ነገ​ሮ​ቹን እን​ሰ​ማ​ለን፤ በሚ​ያ​ደ​ር​ግ​በ​ትስ ጊዜ የነ​ጐ​ድ​ጓ​ዱን ኀይል የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው?”


ጠላ​ቶ​ቼም በላዬ ክፋ​ትን ይና​ገ​ራሉ፦ “መቼ ይሞ​ታል? ስሙስ መቼ ይሻ​ራል?” ይላሉ።


እርሱ ይኖ​ራል፥ ከዓ​ረ​ብም ወር​ቅን ይሰ​ጡ​ታል፤ ሁል​ጊ​ዜም ስለ እርሱ ይጸ​ል​ያሉ፥ ዘወ​ት​ርም ይመ​ር​ቁ​ታል።


ከዚ​ህም ሁሉ በላይ፥ ልጄ ሆይ፥ ተግ​ሣ​ጽን ስማ፥ ፍጻሜ የሌ​ላ​ቸው ብዙ መጻ​ሕ​ፍ​ትን አታ​ድ​ርግ። እጅ​ግም ምር​ምር ሰው​ነ​ትን ያደ​ክ​ማል።


የቤ​ቴ​ልም ካህን አሜ​ስ​ያስ ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ ወደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ልኮ፥ “አሞጽ በእ​ስ​ራ​ኤል ቤት መካ​ከል ዐም​ፆ​ብ​ሃል፤ ምድ​ሪ​ቱም ቃሉን ሁሉ ልት​ሸ​ከም አት​ች​ልም” አለ።


ዕውሮች ያያሉ፤ አንካሶችም ይሄዳሉ፤ ለምጻሞችም ይነጻሉ፤ ደንቆሮችም ይሰማሉ፤ ሙታንም ይነሣሉ፤


ዳግመኛም እላችኋለሁ፤ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል፤” አለ።


ያዩት ሰዎችም አጋንንት ላደሩበት ሰው የሆነውንና ስለ እሪያዎቹ ተረኩላቸው።


ስለ ናዝ​ሬቱ ስለ ኢየ​ሱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ በኀ​ይ​ልም እንደ ቀባው፥ እየ​ዞ​ረም መል​ካም እንደ አደ​ረገ፥ ሰይ​ጣን ያሸ​ነ​ፋ​ቸ​ው​ንም እንደ ፈወሰ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነበ​ርና።


በድ​ካ​ማ​ች​ንና በሥ​ራ​ችን ነዳ​ያ​ንን እን​ቀ​በ​ላ​ቸው ዘንድ እን​ደ​ሚ​ገ​ባን ይህን አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ‘ከሚ​ቀ​በል ይልቅ የሚ​ሰጥ ብፁዕ ነው’ ያለ​ው​ንም የጌ​ታ​ች​ንን የኢ​የ​ሱ​ስን ቃል ዐስቡ።”


እን​ግ​ዲህ ምን እላ​ለሁ? ስለ ጌዴ​ዎን፥ ስለ ባርቅ፥ ስለ ሶም​ሶን፥ ስለ ዮፍ​ታሔ፥ ስለ ዳዊት፥ ስለ ሳሙ​ኤ​ልና ስለ ሌሎች ነቢ​ያት እነ​ግ​ራ​ችሁ ዘንድ ጊዜዬ አጭር ነውና።


跟着我们:

广告


广告