Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 21:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጴጥ​ሮ​ስም መለስ ብሎ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በ​ረ​ውን ያን ደቀ መዝ​ሙር ሲከ​ተ​ለው አየ፤ እር​ሱም ራት ሲበሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ አጠ​ገብ የነ​በ​ረ​ውና “ጌታ ሆይ፥ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥህ ማነው?” ያለው ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ጴጥሮስ ወደ ኋላው ዘወር ሲል፣ ኢየሱስ ይወድደው የነበረ ደቀ መዝሙር ሲከተላቸው አየ፤ ይህም ደቀ መዝሙር ያን ጊዜ እራት ሲበሉ ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ፣ “ጌታ ሆይ፤ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ያለው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጴጥሮስም ዘወር ሲል ኢየሱስ ይወደው የነበረውን ደቀመዝሙር ከበስተኋላው አየ፤ እርሱም በእራት ጊዜ ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ “ጌታ ሆይ! አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ያለው ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ጴጥሮስ ዘወር ብሎ ኢየሱስ የሚወድደው ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ ይህ ደቀ መዝሙር በእራት ጊዜ ወደ ኢየሱስ ተጠግቶ፥ “ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ጴጥሮስም ዘወር ብሎ ኢየሱስ ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር ሲከተለው አየ፤ እርሱም ደግሞ በእራት ጊዜ በደረቱ ተጠግቶ፦ “ጌታ ሆይ፥ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ያለው ነበረ።

参见章节 复制




ዮሐንስ 21:20
6 交叉引用  

ተነሡ፤ እንሂድ፤ እነሆ፥ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቦአል፤” አላቸው።


ፈጥ​ናም ወደ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስና ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው ወደ ነበ​ረው ወደ​ዚያ ወደ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር መጥታ፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው።


ጴጥ​ሮ​ስም እር​ሱን አይቶ፥ “ጌታ ሆይ፥ ይህስ እን​ዴት ይሆ​ናል?” አለው።


ስለ​ዚህ ነገር ምስ​ክር የሆነ፥ ስለ እር​ሱም ይህን የጻፈ ይህ ደቀ መዝ​ሙር ነው፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት እንደ ሆነ እኛ እና​ው​ቃ​ለን።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በረ ያ ደቀ መዝ​ሙ​ርም ለጴ​ጥ​ሮስ፥ “ጌታ​ችን ነው እኮ” አለው፤ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ጌታ​ችን እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ የሚ​ለ​ብ​ሰ​ውን ልብስ አን​ሥቶ በወ​ገቡ ታጠቀ፤ ራቁ​ቱን ነበ​ርና ወደ ባሕር ተወ​ረ​ወረ።


跟着我们:

广告


广告