ዮሐንስ 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ፥ “ሰው ሁሉ መልካሙን የወይን ጠጅ አስቀድሞ ያጠጣል፤ ከጠገቡ በኋላም ተርታውን ያመጣል፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን አቈየህ” አለው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 “ሰው ሁሉ በመጀመሪያ የሚያቀርበው ጥሩውን የወይን ጠጅ ነው፤ እንግዶቹም ብዙ ከጠጡ በኋላ መናኛውን የወይን ጠጅ ያቀርባል፤ አንተ ግን ጥሩውን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቈይተሃል” አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 “ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፤ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል፤” አለው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 “ሰው ሁሉ አስቀድሞ የሚያቀርበው ጥሩውን የወይን ጠጅ ነው፤ ተጋባዦቹ ከጠጡ በኋላ መናኛውን ያቀርባል፤ አንተ ግን ጥሩውን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቈየህ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው። 参见章节 |