ዮሐንስ 19:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 የፋሲካም የመዘጋጀት ቀን ነበር፤ ጊዜዉም ስድስት ሰዓት ያህል ነበር፤ ጲላጦስም አይሁድን፥ “እነሆ፥ ንጉሣችሁ” አላቸው፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ቀኑ የፋሲካ በዓል መዘጋጃ፣ ጊዜውም ከቀኑ ስድስት ሰዓት ያህል ነበር። ጲላጦስም አይሁድን፣ “እነሆ፤ ንጉሣችሁ” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 የፋሲካም በዓል የሚዘጋጅበት ቀን ነበረ፤ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ፤ አይሁድንም “እነሆ ንጉሣችሁ!” አላቸው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 የፋሲካ በዓል የዝግጅት ቀን ነበረ፤ ጊዜውም ወደ ስድስት ሰዓት ገደማ ነበረ፤ በዚያን ጊዜ ጲላጦስ አይሁድን “እነሆ ንጉሣችሁ!” አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ለፋሲካም የማዘጋጀት ቀን ነበረ፤ ስድስት ሰዓትም የሚያህል ነበረ፤ አይሁድንም፦ “እነሆ ንጉሣችሁ” አላቸው። 参见章节 |