Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 18:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ጲላ​ጦ​ስም መልሶ፥ “እኔ አይ​ሁ​ዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳ​ል​ፈው የሰ​ጡህ ወገ​ኖ​ች​ህና ሊቃነ ካህ​ናት አይ​ደ​ሉ​ምን? Aረ ምን አድ​ር​ገ​ሃል?” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ጲላጦስም መልሶ፣ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወደ እኔ የላኩህ የራስህ ወገኖችና የካህናት አለቆች ናቸው፤ ለመሆኑ ምን አድርገህ ነው?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ጲላጦስ መልሶ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል?” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ጲላጦስም “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? አንተን ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ ወገኖችህና የካህናት አለቆች ናቸው፤ ምንድን ነው ያደረግኸው?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ጲላጦስ መልሶ፦ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል?” አለው።

参见章节 复制




ዮሐንስ 18:35
14 交叉引用  

አሁ​ንም ከአ​ንተ ዘንድ የወጡ አይ​ሁድ ወደ እኛ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ መጡ ጌታ​ቸው ንጉሡ ይወቅ፤ ዐመ​ፀ​ኛ​ዪ​ቱ​ንና እጅ​ግም የከ​ፋ​ች​ቱን ከተማ ይሠ​ራሉ፤ ቅጥ​ር​ዋ​ንም ያድ​ሳሉ፤ መሠ​ረ​ቷ​ንም ጠገኑ።


በወ​ን​ድ​ሞ​ቹና በሰ​ማ​ርያ ሠራ​ዊ​ትም ፊት፥ “ከተ​ማ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ እነ​ዚህ ደካ​ሞች አይ​ሁድ ኀይ​ላ​ቸው ምን​ድን ነው? ይተ​ዉ​ላ​ቸ​ዋ​ልን? ይሠ​ዋ​ሉን? በአ​ንድ ቀንስ ይጨ​ር​ሳ​ሉን? የተ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንስ ድን​ጋይ ከፍ​ር​ስ​ራሹ መል​ሰው ያድ​ኑ​ታ​ልን?” ብሎ ተና​ገረ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ከቀ​ያፋ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ወሰ​ዱት፤ አይ​ሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሳይ​በሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ አል​ገ​ቡም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ይህን የም​ት​ና​ገር ከራ​ስህ ነውን? ወይስ ስለ እኔ የነ​ገ​ረህ ሌላ አለን?” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “የእኔ መን​ግ​ሥት ከዚህ ዓለም አይ​ደ​ለ​ችም፤ መን​ግ​ሥ​ቴስ በዚህ ዓለም ብት​ሆን ኖሮ ለአ​ይ​ሁድ እን​ዳ​ል​ሰጥ አሽ​ከ​ሮች በተ​ዋ​ጉ​ልኝ ነበር፤ አሁ​ንም መን​ግ​ሥቴ ከዚህ አይ​ደ​ለ​ችም” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው።


ሊቃነ ካህ​ና​ትና ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ባዩት ጊዜ፥ “ስቀ​ለው! ስቀ​ለው!” እያሉ ጮሁ፤ ጲላ​ጦ​ስም፥ “እና​ንተ ራሳ​ችሁ ውሰ​ዱና ስቀ​ሉት፤ እኔስ በእ​ርሱ ላይ በደል አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም” አላ​ቸው።


“ምና​ል​ባት ከዚህ በፊት ወን​ጀል የሠ​ራ​ህና ከነ​ፍሰ ገዳ​ዮች አራት ሺህ ሰዎ​ችን ይዘህ ወደ ምድረ በዳ የወ​ጣህ ያ ግብ​ፃዊ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አለው።


ስለ ሕጋ​ቸ​ውም ብቻ እንደ ከሰ​ሱት ተረ​ዳሁ፤ ለሞ​ትና ለመ​ታ​ሰር የሚ​ያ​በቃ ሌላ በደል ግን የለ​በ​ትም።


የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆብ አም​ላክ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም አም​ላክ፥ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ የሰ​ጣ​ች​ሁ​ትን፥ እር​ሱም ሊተ​ወው ወዶ ሳለ በጲ​ላ​ጦስ ፊት የካ​ዳ​ች​ሁ​ትን ልጁን ኢየ​ሱ​ስን ገለ​ጠው።


跟着我们:

广告


广告