Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 17:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከክፉ ነገር እን​ድ​ት​ጠ​ብ​ቃ​ቸው ነው እንጂ ከዓ​ለም እን​ድ​ት​ለ​ያ​ቸው አል​ለ​ም​ንም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የምለምንህም ከክፉው እንድትጠብቃቸው እንጂ፣ ከዓለም እንድታወጣቸው አይደለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከክፉው እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም ውጪ እንድትወስዳቸው አለምንም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም።

参见章节 复制




ዮሐንስ 17:15
18 交叉引用  

ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”


ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።


በኀ​ይ​ልህ ሰላም ይሁን፥ በክ​ብ​ርህ ቦታ ደስታ አለ።


ተቸ​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና አቤቱ ይቅር በለኝ፥ ዐይ​ኔም ከቍጣ የተ​ነሣ ታወ​ከች፥ ነፍ​ሴም፥ ሆዴም።


አንተ በም​ት​ሄ​ድ​በት በሲ​ኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕው​ቀ​ትና ጥበብ አይ​ገ​ኙ​ምና እጅህ ለማ​ድ​ረግ የም​ት​ች​ለ​ውን ሁሉ እንደ ኀይ​ልህ አድ​ርግ።


ጻድቅ ሰው እን​ደ​ጠፋ አያ​ችሁ፤ ይህ​ንም በል​ባ​ችሁ አላ​ሰ​ባ​ች​ሁም፤ ጻድ​ቃን ሰዎች ይወ​ገ​ዳሉ፤ ጻድ​ቅም ከክ​ፋት ፊት እንደ ተወ​ገደ ማንም አያ​ስ​ተ​ው​ልም።


ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው።


ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


እኛም የበ​ደ​ለ​ንን ሁሉ ይቅር እን​ድ​ንል በደ​ላ​ች​ንን ይቅር በለን፤ አቤቱ፥ ወደ ፈተና አታ​ግ​ባን፤ ከክፉ ሁሉ አድ​ነን እንጂ።”


እኔ ግን ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ደ​ክም ስለ እና​ንተ ጸለ​ይሁ፤ አን​ተም ተመ​ል​ሰህ ወን​ድ​ሞ​ች​ህን አጽ​ና​ቸው።”


በክፉ ከሚ​ቃ​ወም ከዚህ ዓለም ያድ​ነን ዘንድ በአ​ባ​ታ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ራሱን አሳ​ልፎ ሰጠ።


ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።


ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።


ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።


ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።


跟着我们:

广告


广告