Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 16:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 አሁን አንተ ሁሉን እን​ደ​ም​ታ​ውቅ፥ ማንም ሊነ​ግ​ርህ እን​ደ​ማ​ትሻ ዐወ​ቅን፤ በዚ​ህም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣህ እና​ም​ና​ለን።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 አሁን ሁሉን ነገር እንደምታውቅና ማንም ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ ተረድተናል፤ ይህም ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እንድናምን አድርጎናል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ሁሉንም ነገር እንደምታውቅ፥ እንዲሁም ማንም ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናምናለን፤” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 አንተ ሁሉን እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊያቀርብልህ እንደማያስፈልግህ አሁን ዐወቅን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ወጣህ እናምናለን።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን” አሉት።

参见章节 复制




ዮሐንስ 16:30
12 交叉引用  

ሴቲ​ቱም ኤል​ያ​ስን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው እንደ ሆንህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል በአ​ፍህ እው​ነት እንደ ሆነ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ​ችው።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፥ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድ​ነው?” ተባ​ባሉ።


ያን​ጊ​ዜም እኔን የም​ት​ለ​ም​ኑኝ አን​ዳች የለም፤ እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በስሜ አብን ብት​ለ​ም​ኑት ሁሉን ይሰ​ጣ​ች​ኋል።


ያን​ጊዜ በስሜ ትለ​ም​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም ስለ እና​ንተ አብን እለ​ም​ነ​ዋ​ለህ አል​ላ​ች​ሁም፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ታም​ና​ላ​ች​ሁን?


የሰ​ጠ​ኽ​ኝን ቃል ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ተቀ​ብ​ለው ከአ​ንተ እንደ ወጣሁ በእ​ው​ነት ዐወቁ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ አመኑ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።


አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሥራ ሁሉ ያሳ​የ​ዋል፤ እና​ን​ተም ታደ​ንቁ ዘንድ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ሥራን ያሳ​የ​ዋል።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ​ታ​ችሁ ቢሆ​ንስ እኔን በወ​ደ​ዳ​ች​ሁኝ ነበር፤ እኔ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥቼ መጥ​ቻ​ለ​ሁና፤ እኔ በገዛ እጄ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እርሱ ላከኝ እንጂ።


እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።


跟着我们:

广告


广告