Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 16:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንተ ታለ​ቅ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ታዝ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ፤ ዓለ​ምም ደስ ይለ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ታዝ​ና​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ኀዘ​ና​ችሁ ወደ ደስታ ይለ​ወ​ጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝናላችሁም፤ ዓለም ግን ሐሤት ያደርጋል፤ ይሁን እንጂ ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳለችሁ፤ ሙሾም ታወጣላችሁ፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ትጮኻላችሁም፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተ ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳለችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።

参见章节 复制




ዮሐንስ 16:20
44 交叉引用  

የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞች ደስታ ታላቅ ሰልፍ ነው፥ የዝ​ን​ጉ​ዎ​ችም ደስታ ጥፋት ነው።


በጠ​ላ​ቶቼ ሁሉ ዘንድ ተሰ​ደ​ብሁ፥ ይል​ቁ​ንም በጎ​ረ​ቤ​ቶቼ ዘንድ፥ ለዘ​መ​ዶ​ቼም አስ​ፈሪ ሆንሁ፤ በሜዳ ያዩ​ኝም ከእኔ ሸሹ።


በእ​ጅህ ነፍ​ሴን አደራ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የጽ​ድቅ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ተቤ​ዠኝ።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኔ መል​ሰ​ሃ​ልና፥ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ብለ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለክ​ብሩ የተ​ከ​ላ​ቸው የጽ​ድቅ ዛፎች እን​ዲ​ባሉ ለጽ​ዮን አል​ቃ​ሾች አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በአ​መ​ድም ፋንታ አክ​ሊ​ልን፥ በል​ቅ​ሶም ፋንታ የደ​ስ​ታን ዘይት፥ በኀ​ዘ​ንም መን​ፈስ ፋንታ የም​ስ​ጋ​ናን መጐ​ና​ጸ​ፊያ እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ልኮ​ኛል።


በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።


የተ​ጠ​ማ​ች​ውን ነፍስ ሁሉ አር​ክ​ቻ​ለ​ሁና፥ የተ​ራ​በ​ች​ው​ንም ነፍስ ሁሉ አጥ​ግ​ቤ​አ​ለ​ሁና።


ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ፤’ ተባባሉ።


የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው፤መፅናናትን ያገኛሉና።


ጴጥሮስንም ኢየሱስ “ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ፤” ያለው ቃል ትዝ አለው፤ ነገሩንም አስቦ አለቀሰ።


እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤


ከሚ​ጸ​ል​ይ​በ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ሄደ፤ ከኀ​ዘ​ንም የተ​ነሣ ተኝ​ተው አገ​ኛ​ቸው።


ጴጥ​ሮ​ስም ወደ ውጭ ወጥቶ መራራ ልቅ​ሶን አለ​ቀሰ።


ብዙ ሰዎ​ችም ተከ​ተ​ሉት፤ ሴቶ​ችም “ዋይ ዋይ” እያሉ ያዝ​ኑ​ለ​ትና ያለ​ቅ​ሱ​ለት ነበሩ።


ጌታ​ች​ንም፥ “በት​ካዜ እየ​ሄ​ዳ​ችሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​ነ​ጋ​ገ​ሩት ይህ ነገር ምን​ድን ነው?” አላ​ቸው።


እኛ ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ እና​ደ​ርግ ነበር፤ ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ይህ ነገር ከሆነ ዛሬ ሦስ​ተኛ ቀን ነው።


ዛሬ የም​ት​ራቡ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትጠ​ግ​ባ​ላ​ች​ሁና፤ ዛሬ የም​ታ​ለ​ቅሱ፥ ብፁ​ዓን ናችሁ፤ ትስ​ቃ​ላ​ች​ሁና።


በእ​ኔም ሰላ​ምን እን​ድ​ታ​ገኙ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ፤ በዓ​ለም ግን መከ​ራን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለ​ሙን ድል ነሥ​ቼ​ዋ​ለ​ሁና።”


ነገር ግን ይህን ስለ ነገ​ር​ኋ​ችሁ በል​ባ​ችሁ ኀዘን ሞላ።


ይህ​ንም ብሎ እጆ​ቹ​ንና ጎኑን አሳ​ያ​ቸው፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ጌታ​ች​ንን ባዩት ጊዜ ደስ አላ​ቸው።


እነ​ር​ሱም ከሸ​ን​ጎው ፊት ደስ እያ​ላ​ቸው ወጡ፤ ስለ ስሙ መከራ ይቀ​በሉ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ አድ​ሎ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


በዚህ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በእ​ርሱ ይቅ​ር​ታ​ውን ባገ​ኘ​ን​በት በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​መ​ካ​ለን እንጂ።


ኀዘ​ን​ተ​ኞች ስን​ሆን ዘወ​ትር ደስ​ተ​ኞች ነን፤ እንደ ድሆች ስን​ሆን ብዙ​ዎ​ችን እና​በ​ለ​ጽ​ጋ​ለን፤ ምንም የሌ​ለን ስን​ሆን ሁሉ በእ​ጃ​ችን ነው።


የመ​ን​ፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕ​ግ​ሥት፥ ምጽ​ዋት፥ ቸር​ነት፥ እም​ነት፥ ገር​ነት፥ ንጽ​ሕና ነው።


ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤


ወንድሞቼ ሆይ! የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት፤


ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፤


እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሠቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ላይ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።


ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም አልሆንም፤ ሐዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥


跟着我们:

广告


广告