Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 16:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፥ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድ​ነው?” ተባ​ባሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ፣ “  ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ይሁን እንጂ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ’ እንዲሁም፣ ‘ወደ አብ ስለምሄድ’ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ተባባሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው “ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ ታዩኛላችሁ፤”፥ ደግሞ “ወደ አብ እሄዳለሁና፤ የሚለን ነገር ምንድነው?” ተባባሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶች፥ “ይህ፥ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ አታዩኝም፤ ደግሞ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ፤ ደግሞ ወደ አብ እሄዳለሁ’ የሚለን ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከደቀ መዛሙርቱም አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው፦ “ጥቂት ጊዜ አለ፥ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፥ ታዩኛላችሁ፤ ደግሞ፦ “ወደ አብ እሄዳለሁና” የሚለን ይህ ምንድር ነው?” ተባባሉ።

参见章节 复制




ዮሐንስ 16:17
12 交叉引用  

ቃሉንም ይዘው “ከሙታን መነሣት ምንድር ነው?” እያሉ እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ።


እነርሱም ነገሩን አላስተዋሉም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።


እነ​ርሱ ግን፤ ከተ​ና​ገ​ራ​ቸው ያስ​ተ​ዋ​ሉት የለም፤ ይህ ነገር ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነበ​ርና፤ የተ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አያ​ው​ቁም ነበ​ርና።


እነ​ርሱ ግን ይህን ነገር አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉ​ትም፤ እን​ዳ​ይ​መ​ረ​ም​ሩት ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነውና፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም እን​ዳ​ይ​ጠ​ይ​ቁት ይፈ​ሩት ነበ​ርና።


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አስ​ቀ​ድ​መው ይህን ነገር አላ​ወ​ቁም፤ ነገር ግን ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከከ​በረ በኋላ በዚያ ጊዜ ይህ ነገር ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ፥ ይህ​ንም እንደ አደ​ረ​ጉ​ለት ትዝ አላ​ቸው።


የአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው ያይ​ደለ ይሁ​ዳም፥ “ጌታ ሆይ፥ ለዓ​ለም ያይ​ደለ ለእኛ ራስ​ህን ትገ​ልጥ ዘንድ እን​ዳ​ለህ የተ​ና​ገ​ር​ኸው ምን​ድን ነው?” አለው።


ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ የም​ት​ሄ​ድ​በ​ትን የማ​ና​ውቅ እን​ግ​ዲህ መን​ገ​ዱን እን​ዴት እና​ው​ቃ​ለን?” አለው።


“እን​ዳ​ት​ሰ​ና​ከሉ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ።


“ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና።”


“ይህ ጥቂት የሚ​ለን ምን​ድ​ነው? የሚ​ና​ገ​ረ​ውን አና​ው​ቅም” አሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሊጠ​ይ​ቁት እን​ደ​ሚሹ ዐውቆ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ” ስለ አል​ኋ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ ነገር እርስ በር​ሳ​ችሁ ትመ​ራ​መ​ራ​ላ​ች​ሁን?


አሁን ግን ወደ ላከኝ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ እንኳ፦ ‘ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?’ ብሎ አይ​ጠ​ይ​ቀ​ኝም።


跟着我们:

广告


广告