Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 12:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

50 ትእ​ዛ​ዙም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት እንደ ሆነ አው​ቃ​ለሁ፤ እኔም የም​ና​ገ​ረ​ውን አብ እን​ዳ​ለኝ እን​ዲሁ እና​ገ​ራ​ለሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

50 የርሱ ትእዛዝ ወደ ዘላለም ሕይወት እንደሚያደርስ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህም የምለው ሁሉ አብ እንድናገረው የነገረኝን ብቻ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

50 ትእዛዙም የዘለዓለም ሕይወት እንደ ሆነች አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

50 የእርሱም ትእዛዝ የዘለዓለም ሕይወት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረው አብ የነገረኝን ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

50 ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደ ሆነች አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ የምናገረውን አብ እንደ ነገረኝ እንዲሁ እናገራለሁ።”

参见章节 复制




ዮሐንስ 12:50
12 交叉引用  

ብቻ​ህን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ የሆ​ንህ አን​ተን፥ የላ​ክ​ኸ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ናት።


ነገር ግን ይህ የተ​ጻፈ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እና​ንተ ታምኑ ዘንድ፥ አም​ና​ች​ሁም በስሙ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ነው።


ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወልድ ከራሱ ብቻ ምንም ሊያ​ደ​ርግ አይ​ች​ልም፤ አብ ሲያ​ደ​ርግ ያየ​ውን ነው እንጂ፤ ወል​ድም አብ የሚ​ሠ​ራ​ውን ያንኑ እን​ዲሁ ይሠ​ራል።


ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ መን​ፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አን​ዳች አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ ይህም እኔ የም​ነ​ግ​ራ​ችሁ ቃል መን​ፈስ ነው፤ ሕይ​ወ​ትም ነው።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “አቤቱ፥ የዘ​ለ​ዓ​ለም የሕ​ይ​ወት ቃል እያ​ለህ ወደ ማን እን​ሄ​ዳ​ለን?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የሰ​ውን ልጅ ከፍ ከፍ በአ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ያን​ጊዜ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ አባቴ እንደ አስ​ተ​ማ​ረ​ኝም እን​ዲሁ እና​ገ​ራ​ለሁ እንጂ የም​ና​ገ​ረው ከእኔ አይ​ደ​ለም።


ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስ​ነ​ሣ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ቃሌ​ንም በአፉ አኖ​ራ​ለሁ፤ እንደ አዘ​ዝ​ሁ​ትም ይነ​ግ​ራ​ቸ​ዋል፤


ስለዚህ ግን የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ ያምኑ ዘንድ ላላቸው ሰዎች ምሳሌ እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ ያሳይ ዘንድ ምህረትን አገኘሁ።


እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


跟着我们:

广告


广告