Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 11:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ ወደ መቃ​ብ​ሩም ሄደ፤ መቃ​ብ​ሩም ዋሻ ነበር፤ በላ​ዩም ታላቅ ድን​ጋይ ተገ​ጥ​ሞ​በት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ኢየሱስ ልቡ ዳግመኛ በሐዘን ተነክቶ ወደ መቃብሩ መጣ፤ መቃብሩም በድንጋይ የተገጠመ ዋሻ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ኢየሱስም በድጋሚ በጥልቅ ኀዘን ተውጦ ወደ መቃብሩ መጣ፤ መቃብሩም ዋሻ ነበረ፤ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ኢየሱስ በጣም እያዘነ ወደ መቃብሩ ሄደ፤ መቃብሩ በድንጋይ የተዘጋ ዋሻ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ኢየሱስም በራሱ አዝኖ ወደ መቃብሩ መጣ፤ እርሱም ዋሻ ነበረ፤ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር።

参见章节 复制




ዮሐንስ 11:38
12 交叉引用  

ከዚ​ህም በኋላ አብ​ር​ሃም ኬብ​ሮን በም​ት​ባል በመ​ምሬ ፊት በከ​ነ​ዓን ምድር ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍል በሆ​ነው ዋሻ ውስጥ ሚስ​ቱን ሣራን ቀበረ።


መቃ​ብር በዚያ ያስ​ወ​ቀ​ርህ፥ ከፍ ባለው ስፍራ መቃ​ብር ያሠ​ራህ፥ በድ​ን​ጋ​ይም ውስጥ ለራ​ስህ መኖ​ርያ ያሳ​ነ​ጽህ ወደ​ዚህ ለምን መጣህ? ለም​ንስ በዚህ ተደ​ፋ​ፈ​ርህ?


ስለ​ዚህ አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ወገ​ብ​ህን በማ​ጕ​በጥ አል​ቅስ፤ በፊ​ታ​ቸ​ውም ምርር ብለህ አል​ቅስ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በከ​ተ​ማ​ዪቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መካ​ከል እለፍ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ስለ ተሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱና በሚ​ተ​ክዙ ሰዎች ግን​ባር ላይ ምል​ክት ጻፍ አለው።


ከዐለት በወቀረው በአዲሱ መቃብርም አኖረው፤ በመቃብሩም ደጃፍ ታላቅ ድንጋይ አንከባሎ ሄደ።


እነርሱም ሄደው ከጠባቆች ጋር ድንጋዩን አትመው መቃብሩን አስጠበቁ።


በፍታም ገዝቶ አውርዶም በበፍታ ከፈነው፤ ከዐለትም በተወቀረ መቃብር አኖረው፤ በመቃብሩ ደጃፍም ድንጋይ አንከባለለ።


በመንፈሱም እጅግ ቃተተና “ይህ ትውልድ ስለ ምን ምልክት ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፤ ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም፤” አለ።


ያቺ​ንም ድን​ጋይ ከመ​ቃ​ብሩ ላይ ተን​ከ​ባ​ልላ አገ​ኙ​አት።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እር​ስዋ ስታ​ለ​ቅስ፥ ከእ​ር​ስዋ ጋር የመጡ አይ​ሁ​ድም ሲያ​ለ​ቅሱ ባየ ጊዜ በልቡ አዘነ፤ በራ​ሱም ታወከ።


ከሳ​ም​ን​ቱም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያዉ ቀን ማር​ያም መግ​ደ​ላ​ዊት በማ​ለዳ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃ​ብር መጣች፤ ድን​ጋ​ዩ​ንም ከመ​ቃ​ብሩ አፍ ተነ​ሥቶ አገ​ኘ​ችው።


跟着我们:

广告


广告