Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 11:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ማር​ያ​ምም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ አለ​በት ስፍራ ደረ​ሰ​ችና በአ​የ​ችው ጊዜ ከእ​ግሩ በታች ሰግዳ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኑረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር” አለ​ችው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ማርያምም ኢየሱስ ወደ ነበረበት ቦታ ደርሳ እንዳየችው፣ እግሩ ላይ ተደፍታ፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ፣ ወንድሜ ባልሞተ ነበር” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ “ጌታ ሆይ! አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር፤” አለችው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ማርያም ኢየሱስ ወደ ነበረበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ሥር ወደቀችና “ጌታ ሆይ፥ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ፦ “ጌታ ሆይ፥ አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለችው።

参见章节 复制




ዮሐንስ 11:32
10 交叉引用  

በግ​ን​ባ​ሩም ወድቆ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና አመ​ሰ​ገ​ነው፤ ሰው​የ​ውም ሳም​ራዊ ነበር።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ይህን አይቶ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ እግር በታች ሰገ​ደና፥ “እኔ ኀጢ​አ​ተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።


እነ​ሆም ኢያ​ኢ​ሮስ የሚ​ባል ሰው መጣ፤ እር​ሱም የም​ኵ​ራብ ሹም ነበር፤ ከጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ እግር በታ​ችም ሰገደ። ወደ ቤቱም ይገባ ዘንድ ለመ​ነው።


ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር።


ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን እን​ዲህ አለ​ችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በዚህ ኖረህ ቢሆን ወን​ድሜ ባል​ሞ​ተም ነበር።


ከእ​ነ​ር​ሱም መካ​ከል፥ “ዕዉር ሆኖ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ዐይን ያበ​ራው ይህ ሰው ይህስ እን​ዳ​ይ​ሞት ሊያ​ደ​ርግ ባል​ቻ​ለም ነበ​ርን?” ያሉ ነበሩ።


ያም የን​ጉሥ ወገን የሆነ ሰው፥ “አቤቱ፥ ልጄ ሳይ​ሞት ፈጥ​ነህ ውረድ” አለው።


ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።


አራቱም እንስሶች ‘አሜን’ አሉ፤ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።


መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ እንስሶችና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ።


跟着我们:

广告


广告