Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 11:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ይህ​ንም ብላ ሄደች፤ እኅ​ቷን ማር​ያ​ም​ንም ቀስ ብላ ጠራ​ችና፥ “እነሆ፥ መም​ህ​ራ​ችን መጥቶ ይጠ​ራ​ሻል” አለ​ቻት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ይህን ካለች በኋላ፣ ተመልሳ እኅቷን ማርያምን ለብቻዋ ጠርታ፣ “መምህሩ መጥቷል፤ ይፈልግሻልም” አለቻት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ይህንም ብላ ሄደች፤ እኅትዋንም ማርያምን በስውር ጠርታ “መምህር መጥቷል፤ እየጠራሽም ነው፤” አለቻት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ማርታ ይህን ከተናገረች በኋላ ሄደችና እኅትዋን ማርያምን “መምህር መጥቶአል፤ አንቺንም ይጠራሻል” ብላ በስውር ጠራቻት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ይህንም ብላ ሄደች እኅትዋንም ማርያምን በስውር ጠርታ፦ “መምህሩ መጥቶአል ይጠራሽማል” አለቻት።

参见章节 复制




ዮሐንስ 11:28
19 交叉引用  

በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እያንዳንዱ ከወይኑና ከበለሱ በታች ሆኖ ባልንጀራውን ይጠራል።


እርሱም “ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ ‘መምህር ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ ይላል’ በሉት፤” አለ።


ኢየሱስም ቆመና “ጥሩት” አለ። ዕውሩንም “አይዞህ፤ ተነሣ፤ ይጠራሃል፤” ብለው ጠሩት።


የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ ‘መምህሩ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው? ይላል፤’ በሉት።


የዚ​ያን ቤት ጌታ፦ መም​ህር ከደቀ መዛ​ሙ​ርቴ ጋር የፋ​ሲ​ካን በግ የም​በ​ላ​በት ቤት ወዴት ነው? ብሎ​ሃል በሉት።


ከዮ​ሐ​ንስ ዘንድ ሰም​ተው ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ከተ​ከ​ተ​ሉት ከሁ​ለ​ቱም አንዱ የስ​ም​ዖን ጴጥ​ሮስ ወን​ድም እን​ድ​ር​ያስ ነበር።


ፊል​ጶስ ግን ከእ​ን​ድ​ር​ያ​ስና ከጴ​ጥ​ሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበር።


ለእ​ርሱ በረ​ኛው ይከ​ፍ​ት​ለ​ታል፤ በጎ​ቹም ቃሉን ይሰ​ሙ​ታል፤ እር​ሱም በጎ​ቹን በየ​ስ​ማ​ቸው ይጠ​ራ​ቸ​ዋል፤ አው​ጥ​ቶም ያሰ​ማ​ራ​ቸ​ዋል።


ማር​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እንደ መጣ በሰ​ማች ጊዜ ወጥታ ተቀ​በ​ለ​ችው፤ ማር​ያም ግን በቤት ተቀ​ምጣ ነበር።


እር​ስ​ዋም ይህን በሰ​ማች ጊዜ ፈጥና ተነ​ሣች፤ ወደ እር​ሱም ሄደች።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ማርታ በተ​ቀ​በ​ለ​ች​በት ስፍራ ነበረ እንጂ ገና ወደ መን​ደር አል​ገ​ባም ነበር።


እና​ንተ ‘መም​ህ​ራ​ችን፥ ጌታ​ች​ንም’ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካም ትላ​ላ​ችሁ፤ እኔ እን​ዲሁ ነኝና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ማር​ያም!” አላት፤ እር​ስ​ዋም መለስ ብላ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ፥ “ረቡኒ!” አለ​ችው፤ ትር​ጓ​ሜ​ዉም “መም​ህር” ማለት ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ይወ​ደው የነ​በረ ያ ደቀ መዝ​ሙ​ርም ለጴ​ጥ​ሮስ፥ “ጌታ​ችን ነው እኮ” አለው፤ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ጌታ​ችን እንደ ሆነ በሰማ ጊዜ የሚ​ለ​ብ​ሰ​ውን ልብስ አን​ሥቶ በወ​ገቡ ታጠቀ፤ ራቁ​ቱን ነበ​ርና ወደ ባሕር ተወ​ረ​ወረ።


ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።


ስለ​ዚ​ህም የላ​ሉ​ትን እጆች፥ የሰ​ለ​ሉ​ት​ንም ጕል​በ​ቶች አቅኑ።


跟着我们:

广告


广告