Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዮሐንስ 1:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በዓ​ለም ነበረ፤ ዓለ​ሙም በእ​ርሱ ሆነ፤ ዓለሙ ግን አላ​ወ​ቀ​ውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እርሱ በዓለም ውስጥ ነበረ፤ ዓለም የተፈጠረው በርሱ ቢሆንም እንኳ፣ ዓለም አላወቀውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በዓለም ነበረ፤ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፤ ዓለም ግን አላወቀውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እርሱም በዓለም ነበረ፤ ዓለምም የተፈጠረው በእርሱ ነው፤ ዓለም ግን አላወቀውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።

参见章节 复制




ዮሐንስ 1:10
23 交叉引用  

አጋ​ርም ይና​ገ​ራት የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራ​ራ​ህ​ልኝ አንተ ነህ፤ የተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ኝን በፊቴ አይ​ች​ዋ​ለ​ሁና።”


ከዚ​ህም በኋላ አብ​ራም የዘ​ጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው “በፊ​ትህ የሄ​ድሁ ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መል​ካም አድ​ርግ፤ ንጹ​ሕም ሁን፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ንግ​ግ​ሩን በጨ​ረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።


መል​ኩም የተ​ናቀ፥ ከሰ​ውም ልጆች ሁሉ የተ​ዋ​ረደ፥ የተ​ገ​ረፈ ሰው፥ መከ​ራ​ንም የተ​ቀ​በለ ነው፤ ፊቱ​ንም መል​ሶ​አ​ልና አቃ​ለ​ሉት፥ አላ​ከ​በ​ሩ​ት​ምም።


ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


ወደ ወገ​ኖቹ መጣ፤ ወገ​ኖቹ ግን አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​ትም።


በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።


ሁሉም በእ​ርሱ ሆነ፤ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም።


ብር​ሃ​ንም በጨ​ለማ ያበ​ራል፤ ጨለ​ማም አላ​ገ​ኘ​ውም።


ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላ​ወ​ቀ​ህም፤ እኔ ግን ዐወ​ቅ​ሁህ፤ እነ​ዚ​ህም አንተ እንደ ላክ​ኸኝ ዐወቁ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “አባቴ እስከ ዛሬ ይሠ​ራል፤ እኔም እሠ​ራ​ለሁ” አላ​ቸው።


ከዚ​ህም ሁሉ ጋር መል​ካም ሥራን እየ​ሠራ ከሰ​ማይ ዝና​ምን፥ ፍሬ የሚ​ሆ​ን​በ​ት​ንም ወራት ሲሰ​ጠን፥ ልባ​ች​ን​ንም በመ​ብ​ልና በደ​ስታ ሲሞ​ላው ራሱን ያለ ምስ​ክር አል​ተ​ወም።”


ሰዎች በጥ​በ​ባ​ቸው በማ​ያ​ው​ቁት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ስን​ፍና በሚ​መ​ስ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ያመ​ኑ​ትን ሊያ​ድ​ና​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወድ​ዶ​አ​ልና።


የዚህ ዓለም ሹሞ​ችም አላ​ወ​ቁ​ትም፤ ይህ​ንስ ቢያ​ውቁ ኑሮ የክ​ብር ባለ​ቤ​ትን ባል​ሰ​ቀ​ሉ​ትም ነበር።


ለእ​ኛስ ሁሉ ከእ​ርሱ የሆነ፥ እኛም ለእ​ርሱ የሆን አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእ​ርሱ የሆነ፥ እኛም በእ​ርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም አለን።


በእ​ርሱ ቃል​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ፈጥ​ሮ​አ​ልና በሰ​ማይ ያለ​ውን፥ በም​ድ​ርም ያለ​ውን፥ የሚ​ታ​የ​ው​ንና የማ​ይ​ታ​የ​ውን፥ መና​ብ​ር​ትም ቢሆኑ፥ አጋ​እ​ዝ​ትም ቢሆኑ፥ መኳ​ን​ን​ትም ቢሆኑ፥ ቀደ​ም​ትም ቢሆኑ፥ ሁሉን በእ​ርሱ ቃል​ነት ፈጥ​ሮ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ለእ​ርሱ ተፈ​ጠረ፤


ዓለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ተፈ​ጠረ፥ የሚ​ታ​የ​ውም ነገር ከማ​ይ​ታ​የው እንደ ሆነ በእ​ም​ነት እና​ው​ቃ​ለን።


የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።


跟着我们:

广告


广告