Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 8:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​መፅ ይፈ​ር​ዳ​ልን? ሁሉን የፈ​ጠረ አም​ላ​ክስ ጽድ​ቅን ያጣ​ም​ማ​ልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር ፍትሕን ያጣምማልን? ሁሉን ቻይ አምላክስ ጽድቅን ያጣምማልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በውኑ እግዚአብሔር ፍርድን ያጣምማልን? ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር ፍርድን ከቶ አያጣምምም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ሁልጊዜ ትክክለኛውን ነገር ያደርጋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በውኑ እግዚአብሔር ፍርድን ያጣምማልን? ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?

参见章节 复制




ኢዮብ 8:3
29 交叉引用  

አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።”


አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ላይ ይሁን፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በደ​ልና ለሰው ፊት ማድ​ላት፥ መማ​ለ​ጃም መው​ሰድ የለ​ምና ሁሉን ተጠ​ን​ቅ​ቃ​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።


ኀጢ​ኣ​ተኛ ብሆን በአ​ንተ ዘንድ መል​ካም ነውን? የእ​ጅ​ህን ሥራ ቸል ብለ​ሃ​ልና፤ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ምክር ተመ​ል​ክ​ተ​ሃ​ልና።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ከኝ፥ መዓ​ቱ​ንም በእኔ ላይ እንደ አበዛ ዕወቁ።


እነሆ፥ በዘ​ለፋ እደ​ክ​ማ​ለሁ፤ አል​ና​ገ​ር​ምም፤ አሰ​ም​ቼም እጮ​ኻ​ለሁ፤ ነገር ግን ፍርድ የለ​ኝም።


እን​ገ​ዛ​ለ​ትስ ዘንድ እርሱ ምን ይች​ላል? ወይስ ወደ እርሱ ብን​ቀ​ርብ ምን ይጠ​ቅ​መ​ናል?


ዐይ​ኖቹ ልጆቹ ሲወጉ ያያሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አያ​ድ​ና​ቸ​ውም።


ኢዮብ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፦ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ፍር​ዴን አስ​ወ​ገደ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ው​ነት ክፉ ነገ​ርን ሊያይ አይ​ወ​ድም። እርሱ ሁሉን የሚ​ችል ዐዋቂ አም​ላክ ነውና።


ሥራ​ው​ንስ የሚ​መ​ረ​ምር ማን ነው? ወይስ፦ ክፉ ሠር​ተ​ሃል የሚ​ለው ማን ነው?


ዕው​ቀ​ቴን ከሩቅ አመ​ጣ​ለሁ፥ ሥራ​ዬ​ንም እው​ነት ነው እላ​ለሁ።


በኀ​ይል ከእ​ርሱ ጋር እኩል የሚ​ሆን፥ እው​ነ​ት​ንም የሚ​ፈ​ርድ ሌላ አና​ገ​ኝም። እርሱ እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ታስ​ባ​ለ​ህን?


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንጹሕ የሚ​ሆን ሟች ማን ነው? በሥ​ራ​ውስ የሚ​ጸ​ድቅ ሰው ማን ነው?


“በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን? ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”


ወይም ፍር​ዴን መቃ​ወ​ም​ህን ተው፥ ጽድ​ቅህ እን​ድ​ት​ገ​ለጥ እንጂ እኔ በሌላ መን​ገድ የም​ፈ​ር​ድ​ብህ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን?


“በእ​ው​ነት እን​ዲህ እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ፤ ሰውስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድቅ መሆን እን​ዴት ይች​ላል?


በማ​ለዳ ምሕ​ረ​ት​ህን እን​ጠ​ግ​ባ​ለ​ንና፤ በዘ​መ​ና​ችን ሁሉ ደስ ይለ​ናል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን።


ወደ ደጆቹ በመ​ገ​ዛት፥ ወደ አደ​ባ​ባ​ዮ​ቹም በም​ስ​ጋና ግቡ፤ አመ​ስ​ግ​ኑት፥ ስሙ​ንም አክ​ብሩ፥


“እና​ንተ ግን፦ የጌታ መን​ገድ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ችም ትላ​ላ​ችሁ። የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስሙ፤ በውኑ መን​ገዴ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ይል​ቅስ የእ​ና​ንተ መን​ገድ ያል​ቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን?


“የሕ​ዝ​ብህ ልጆች፦ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም ይላሉ፤ ነገር ግን የእ​ነ​ርሱ መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም።


እና​ንተ ግን፦ የጌታ መን​ገድ የቀና አይ​ደ​ለም ትላ​ላ​ችሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ላይ እንደ መን​ገ​ዳ​ችሁ እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።”


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሥ​ራው እው​ነ​ተኛ ነው፤ መን​ገ​ዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ክፋ​ትም የለ​በ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቅና ቸር ነው።


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


ከመሰዊያውም “አዎን፤ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ፍርዶችህ እውነትና ጽድቅ ናቸው፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告