Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 7:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 የሰ​ውን ልብ፦ የም​ታ​ውቅ ሆይ፥ በድ​ዬስ እንደ ሆነ እን​ግ​ዲህ ምን ላደ​ር​ግ​ልህ እች​ላ​ለሁ? ስለ​ምን እኔን ለመ​ከራ አደ​ረ​ግ​ኸኝ? ስለ ምን በአ​ንተ ላይ እን​ድ​ና​ገር በአ​ም​ሳ​ልህ ፈጠ​ር​ኸኝ? ስለ ምንስ እኔ ሸክም ሆን​ሁ​ብህ?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሰውን የምትከታተል ሆይ፤ ኀጢአት ብሠራ፣ አንተን ምን አደርግሃለሁ? ለምን ዒላማህ አደረግኸኝ? ለምንስ ሸክም ሆንሁብህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደሆነ ምን ላድርግልህ? ስለምን እኔን ዒላማ አደረግኸኝ? ስለምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 አንተ ሰዎችን በመቈጣጠር የምትከታተል አምላክ ሆይ፥ እኔ ኃጢአት በመሥራቴ አንተ ምን ተበደልክ? ስለምን ዒላማ አደረግኸኝ? ይህን ያኽል ከባድ ሸክም ሆንኩብህን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ በድዬስ እንደ ሆነ ምን ላድርግልህ? ስለ ምን እኔን ለአንተ ዓላማ አደረግኸኝ? ስለ ምን እኔ ሸክም ሆንሁብህ?

参见章节 复制




ኢዮብ 7:20
21 交叉引用  

ዕዝ​ራም እን​ዲህ አለ፥ “አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ ሰማ​ዩ​ንና የሰ​ማ​ያት ሰማ​ይን፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ ምድ​ር​ንና በእ​ር​ስዋ ላይ ያሉ​ትን ሁሉ፥ ባሕ​ሮ​ቹ​ንና በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ሁሉ​ንም ሕያው አድ​ር​ገ​ኸ​ዋል፤ የሰ​ማ​ዩም ሠራ​ዊት ለአ​ንተ ይሰ​ግ​ዳሉ።


ኀጢ​ኣት ብሠራ አንተ ትጠ​ባ​በ​ቀ​ኛ​ለህ፤ ከኀ​ጢ​ኣ​ቴም ንጹሕ አታ​ደ​ር​ገ​ኝም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ እለ​ዋ​ለሁ፦ ኀጢ​ኣ​ተኛ እን​ድ​ሆን አታ​ስ​ተ​ም​ረኝ፤ ለም​ንስ እን​ደ​ዚህ ፈረ​ድ​ህ​ብኝ?


ክፋ​ቴን ትፈ​ላ​ለግ ዘንድ፥ ኀጢ​ኣ​ቴ​ንም ትመ​ረ​ምር ዘንድ፥


ክፉ ነገ​ርን ጽፈ​ህ​ብ​ኛ​ልና፤ የል​ጅ​ነ​ቴ​ንም ኀጢ​አት ተቈ​ጣ​ጥ​ረህ አስ​ታ​ጥ​ቀ​ኸ​ኛ​ልና።


አሁን ግን ኀጢ​አ​ቶ​ችን ቈጥ​ረ​ሃል፤ ከበ​ደ​ሌም እን​ዲ​ቱ​ንስ እንኳ አል​ረ​ሳ​ህም።


“ክፋ​ት​ህስ የበዛ አይ​ደ​ለ​ምን? ኀጢ​አ​ት​ህስ ቍጥር የሌ​ለው አይ​ደ​ለ​ምን?


ከአ​ዝ​መ​ራዬ በፊት ልቅ​ሶዬ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ ስለ ደረ​ሰ​ብ​ኝም አስ​ፈሪ ነገር ሁል​ጊዜ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።


ታላቅ በደ​ልም በድዬ እንደ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ቴ​ንም ሰውሬ እንደ ሆነ፥


ያን​ጊ​ዜም ሰው ራሱን ይነ​ቅ​ፋል፤ እን​ዲ​ህም ይላል፦ ‘እኔ ምን አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ? እንደ ኀጢ​አ​ቶ​ችም መጠን አል​ቀ​ጣ​ኝም፤


እኔ ንጹሕ ነኝ፥ አል​በ​ደ​ል​ሁ​ምና፤ እኔ ጻድቅ ነኝ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም አል​ሠ​ራ​ሁም።


ኀጢ​አት ብሠ​ራስ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ? ትላ​ለህ።


ኀጢ​አት ብት​ሠራ በእ​ርሱ ላይ ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ብዙም ብት​በ​ድል ምን ማድ​ረግ ትች​ላ​ለህ?


እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍላጻ በሥ​ጋዬ ላይ ነው፤ መር​ዙም ደሜን ይመ​ጥ​ጣል። ለመ​ና​ገር ስጀ​ም​ርም ይወ​ጋ​ኛል።


ብዙ በሬ​ዎች ከበ​ቡኝ፥ የሰ​ቡ​ትም ፍሪ​ዳ​ዎች ያዙኝ፤


ጽድ​ቅ​ህን እንደ ብር​ሃን፥ ፍር​ድ​ህ​ንም እንደ ቀትር ያመ​ጣ​ታል።


ለእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐቱ ነውና፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ፍርድ ነውና።


ቀስ​ቱን ገተረ፤ ለፍ​ላ​ጻ​ውም እንደ ዒላማ አደ​ረ​ገኝ።


跟着我们:

广告


广告