Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 40:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን? ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ከሁሉን ቻይ አምላክ ጋራ ተከራክሮ የሚረታው አለን? እግዚአብሔርን የሚወቅሥ እርሱ መልስ ይስጥ!”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን የሚችል አምላክን መተቸት ይችላልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ኢዮብ ሆይ! ለመሆኑ ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ተከራክሮ ሊረታ የሚችል ይመስልሃልን? ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር የምትከራከር አንተ ስለ ሆንክ፥ እስቲ መልስ ስጥ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።

参见章节 复制




ኢዮብ 40:2
35 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ እለ​ዋ​ለሁ፦ ኀጢ​ኣ​ተኛ እን​ድ​ሆን አታ​ስ​ተ​ም​ረኝ፤ ለም​ንስ እን​ደ​ዚህ ፈረ​ድ​ህ​ብኝ?


ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ከፈ​ቀ​ደም በፊቱ እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።


የሠ​ራ​ሁት ቢኖር ይነ​ግ​ረኝ ነበረ፥ ስከ​ራ​ከ​ርም አፌ ዝም አይ​ልም ነበር።


“እን​ደ​ዚህ የፈ​ረ​ደ​ብኝ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ነፍ​ሴ​ንም መራራ ያደ​ረገ ሁሉን የሚ​ችል ሕያው አም​ላ​ክን!


በመ​ራ​ራ​ነት ላሉት ብር​ሃን፥ በነ​ፍስ ለተ​ጨ​ነ​ቁ​ትም ሕይ​ወት፥


ሞት ለሰው ዕረ​ፍቱ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ከለ​ከ​ለው።


ምሕ​ረት የሌ​ላ​ቸው ሰዎች ደበ​ደ​ቡኝ፥ የገ​ረ​ፈ​ችኝ እጅም በረ​ታች።


የሚ​ያ​ደ​ም​ጠ​ኝን ማን በሰ​ጠኝ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጅ አል​ፈ​ራሁ እንደ ሆነ፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ር​ድ​ብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖ​ረኝ!


አንተ፦ ‘ቃሌን ሁሉ ለምን አይ​ሰ​ማ​ኝም?’ ትላ​ለህ።


እን​ግ​ዲህ እንደ ሰው ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፥ አን​ተም መል​ስ​ልኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መለሰ፥ ኢዮ​ብ​ንም እን​ዲህ አለው፦


ኢዮ​ብም መለሰ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እን​ዲህ አለው፦


ጠባቂ አዝ​ዘ​ህ​ብ​ኛ​ልና፥ እኔ ባሕር ወይስ አን​በሪ ነኝን?


ከእ​ርሱ ጋር ይከ​ራ​ከር ዘንድ ቢወ​ድድ፥ ከሺህ ነገር አን​ዱን መመ​ለስ አይ​ች​ልም።


የሆ​ነው ሁሉ እነሆ፥ ስሙ አስ​ቀ​ድሞ ተጠራ፥ ሰውም እንደ ሆነ ታወቀ፤ ከእ​ር​ሱም ከሚ​በ​ረ​ታው ጋር ይፋ​ረድ ዘንድ አይ​ች​ልም።


ወይስ ከማን ጋር ተመ​ካ​ከረ? ወይስ ማን መከ​ረው? ፍር​ድ​ንስ ማን አስ​ተ​ማ​ረው? የጥ​በ​ብ​ንስ መን​ገድ ማን አሳ​የው?


የሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእ​ኔስ ጋር የሚ​ከ​ራ​ከር ማን ነው? እስቲ በእኔ ላይ ይነሣ፤ የሚ​ከ​ራ​ከ​ረ​ኝስ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅ​ረብ።


ባቢ​ሎን ሆይ! በመ​ከ​ራው ተይ​ዘሽ ጠፋሽ፤ አን​ቺም ይህ እን​ደ​መ​ጣ​ብሽ አላ​ወ​ቅ​ሽም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​መ​ሽ​ዋ​ልና ተገ​ኝ​ተ​ሻል፤ ተይ​ዘ​ሽ​ማል።


“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፦ ‘አባ​ቶች ጨርቋ የወ​ይን ፍሬ በሉ፥ የል​ጆ​ችም ጥር​ሶች ጠረሱ’ ብላ​ችሁ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የም​ት​መ​ስ​ሉት ምሳሌ ምን​ድን ነው?


ተቀብለውም ‘እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፤ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው፤’ ብለው በባለቤቱ ላይ አንጕኦራጕኦሩ።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​ስ​ቀ​ና​ውን? በውኑ እኛ ከእ​ርሱ እን​በ​ረ​ታ​ለን?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳብ ማን ያው​ቃል? መካ​ሩስ ማን ነው? እኛ ግን ክር​ስ​ቶስ የሚ​ገ​ል​ጠው ዕው​ቀት አለን።


跟着我们:

广告


广告