Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 40:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የቍ​ጣ​ህን መላ​እ​ክት ላክ፤ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ው​ንም ሁሉ አዋ​ር​ደው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ቍጣህን አፍስስ፤ ትዕቢተኛውን ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የቁጣህን ሙላት አፍስስ፥ ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ትዕቢተኞችን ተመልክተህ አዋርዳቸው፤ ቊጣህንም በላያቸው አፍስስ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የቍጣህን ፈሳሽ አፍስስ፥ ትዕቢተኛውንም ሁሉ ተመልክተህ አዋርደው።

参见章节 复制




ኢዮብ 40:11
34 交叉引用  

“ሆዱን ቢያ​ጠ​ግብ፥ የመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍት ይጨ​መ​ር​በ​ታል፤ የሕ​ማ​ሙም ሥቃይ ይጸ​ና​በ​ታል።


ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ክፉ ቀን ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለች፤ በቍጣ ቀንም ይወ​ስ​ዱ​ታል።


በእ​ር​ሱም ላይ የማ​ያ​ው​ቀው ይመ​ጣ​በ​ታል፤ አይ​ራ​ራ​ለ​ትም፥ ከእ​ጁም ፈጥኖ መሸሽ ይወ​ድ​ዳል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጠ​ፋሉ፥ በቍ​ጣ​ውም መን​ፈስ ያል​ቃሉ።


ተራ​ሮ​ችን ይነ​ቅ​ላል፤ አያ​ው​ቁ​ት​ምም፤ በቍ​ጣ​ውም ይገ​ለ​ብ​ጣ​ቸ​ዋል።


“ኀይ​ልህ ግሩም ነው” ይላሉ፥ ግር​ማ​ህ​ንም ይነ​ጋ​ገ​ራሉ፥ ብር​ታ​ት​ህ​ንም ያስ​ረ​ዳሉ።


በእ​ም​ነት ወደ ፊቱ እን​ድ​ረስ፥ በዝ​ማ​ሬም ለእ​ርሱ እልል እን​በል፤


አቤቱ፥ ቀኝህ በኀ​ይል ከበረ፤ አቤቱ፥ ቀኝህ ጠላ​ቶ​ችን አደ​ቀቀ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፃ​ው​ያን ከሚ​መ​ኩ​ባ​ቸ​ውና ከሚ​ገ​ዙ​ላ​ቸው አማ​ል​ክት ሁሉ እን​ዲ​በ​ልጥ አሁን ዐወ​ቅሁ” አለ።


ሰውም ሁሉ ይዋ​ረ​ዳል፤ የሰ​ውም ኵራት ይወ​ድ​ቃል፤ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።


ከአ​ዛ​ዥ​ነት ሥራ​ህና ከሥ​ል​ጣ​ንህ ትሻ​ራ​ለህ።


የክ​ቡ​ራ​ንን ትዕ​ቢት ይሽር ዘንድ፥ የም​ድ​ር​ንም ክቡ​ራን ሁሉ ያዋ​ርድ ዘንድ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስ​ኖ​ታል።


እርሱ ክፉ እንደ አደ​ረ​ገና እንደ አጠፋ በእ​ርሱ ላይ እጁን ያነ​ሣል፤ በእ​ር​ሱም ላይ እጁን ያነ​ሣው ስድ​ብን ይሽ​ራል።


በከ​ፍታ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሰዎች ዝቅ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የተ​መ​ሸ​ጉ​ት​ንም ከተ​ሞች ትጥ​ላ​ለህ፤ እስከ ምድ​ርም ድረስ ታወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ።


ስለ​ዚህ የቍ​ጣ​ውን መዓ​ትና የሰ​ል​ፉን ጽናት አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ በዙ​ሪ​ያ​ቸው አቃ​ጠ​ላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን አላ​ወ​ቁም፤ በል​ባ​ቸ​ውም አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም።


የሞ​አ​ብን ስድብ፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንም ብዙ ውር​ደ​ቱን፥ ልቡ​ና​ው​ንም ያስ​ታ​በ​የ​በ​ትን ትዕ​ቢ​ቱን ሰም​ተ​ናል።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢ​ሮ​ስን አለቃ እን​ዲህ በለው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ልብህ ኰር​ት​ዋል፥ አንተ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሕር መካ​ከል እን​ዲ​ቀ​መጥ እኔም ተቀ​ም​ጫ​ለሁ ብለ​ሃ​ልና፤ አንተ ሰው ስት​ሆን ልብ​ህን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብ ብታ​ደ​ር​ግም አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ህም።


በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቆች ተሰነጠቁ።


ስፍራዋን ግን በሚያጥለቀልቅ ጎርፍ ፈጽሞ ያጠፋታል፥ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።


እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፣ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፣ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመ​ለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ይዋ​ረ​ዳ​ልና፤ ራሱ​ንም የሚ​ያ​ዋ​ርድ ይከ​ብ​ራ​ልና።”


እሳት ከቍ​ጣዬ ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃ​ጥ​ላ​ለች፤ ምድ​ር​ንም ከፍ​ሬዋ፤ ጋር ትበ​ላ​ለች፤ የተ​ራ​ሮ​ችን መሠ​ረት ታነ​ድ​ዳ​ለች።


ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል፤” ይላል።


跟着我们:

广告


广告