Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 4:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንጹሕ የሚ​ሆን ሟች ማን ነው? በሥ​ራ​ውስ የሚ​ጸ​ድቅ ሰው ማን ነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ‘ሥጋ ለባሽ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን? ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹሕ ሊሆን ይችላልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ‘በውኑ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን፥ ወይስ ሰው በፈጣሪው ፊት ሊነጻ ይችላልን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ‘በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ሊገኝ የሚችል ሰው አለን? ወይስ በፈጣሪው ፊት ንጹሕ የሚሆን ሰው ይገኛልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በውኑ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን፥ ወይስ ሰው በፈጣሪው ፊት ሊነጻ ይችላልን?

参见章节 复制




ኢዮብ 4:17
25 交叉引用  

አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።”


ከር​ኵ​ሰት የሚ​ነጻ ማን ነው? አንድ ስንኳ የለም።


ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች ሰው ማን ነው? ጻድ​ቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተ​ወ​ለደ ማን ነው?


ጻድቅ ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዴት ንጹሕ ይሆ​ናል? ከሴ​ትስ የተ​ወ​ለደ ራሱን ንጹሕ ማድ​ረግ እን​ዴት ይች​ላል?


እኔን በማ​ኅ​ፀን የፈ​ጠረ እነ​ር​ሱ​ንስ የፈ​ጠረ አይ​ደ​ለ​ምን? በማ​ኅ​ፀ​ንስ ውስጥ የሠ​ራን አንድ አይ​ደ​ለ​ምን?


ለሰው ፊት ማድ​ላ​ትን አላ​ው​ቅም፤ ከሰ​ውም የተ​ነሣ የማ​ፍ​ረው ካለ ትሎች ይብ​ሉኝ።


ነገር ግን በሌ​ሊት ጥበ​ቃን የሚ​ያ​ዝዝ ፈጣ​ሪዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት ነው? የሚል የለም፤


“አንተ ተዋ​ቅ​ሰህ ምን ትላ​ለህ? ወይስ፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ የም​ትል አንተ ማን ነህ?


ዕው​ቀ​ቴን ከሩቅ አመ​ጣ​ለሁ፥ ሥራ​ዬ​ንም እው​ነት ነው እላ​ለሁ።


ተነ​ሣሁ፤ ነገር ግን አላ​ወ​ቅ​ሁም፥ ተመ​ለ​ከ​ትሁ፥ በዐ​ይ​ኖ​ቼም ፊት መልክ አል​ነ​በ​ረም። ነገር ግን ጥላን አያ​ለሁ፤ ድም​ፅ​ንም እሰ​ማ​ለሁ፦


ወይም ፍር​ዴን መቃ​ወ​ም​ህን ተው፥ ጽድ​ቅህ እን​ድ​ት​ገ​ለጥ እንጂ እኔ በሌላ መን​ገድ የም​ፈ​ር​ድ​ብህ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን?


በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​መፅ ይፈ​ር​ዳ​ልን? ሁሉን የፈ​ጠረ አም​ላ​ክስ ጽድ​ቅን ያጣ​ም​ማ​ልን?


“በእ​ው​ነት እን​ዲህ እንደ ሆነ ዐወ​ቅሁ፤ ሰውስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ጻድቅ መሆን እን​ዴት ይች​ላል?


የሚ​ም​ረኝ፥ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አዳኜ፤ መታ​መ​ኛ​ዬም፤ እር​ሱን ታመ​ንሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእኔ በታች የሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ልኝ።


በም​ድር ላይም መል​ካ​ምን የሚ​ሠራ ኀጢ​አ​ት​ንም የማ​ያ​ደ​ርግ ጻድቅ ሰው አይ​ገ​ኝ​ምና።


አቤቱ! ከአ​ንተ ጋር በተ​ም​ዋ​ገ​ትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ጋር ስለ ፍርድ ልና​ገር። የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች መን​ገድ ስለ ምን ይቀ​ናል? በደ​ል​ንስ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላ​ቸ​ዋል?


“የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ጥልቅ ነው፤ ማንስ ያው​ቀ​ዋል?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባለ​ጠ​ግ​ነት፥ ጥበ​ብና ዕው​ቀት እን​ዴት ጥልቅ ነው! ለመ​ን​ገ​ዱም ፍለጋ የለ​ውም፤ ፍር​ዱ​ንም የሚ​ያ​ው​ቀው የለም።


ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ።


ሰው ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ከ​ራ​ከ​ረው አንተ ምን​ድን ነህ? ሥራ ሠሪ​ውን እን​ዲህ አታ​ድ​ር​ገኝ ሊለው ይች​ላ​ልን?


አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።


跟着我们:

广告


广告