26 ማንም በሌለበት ምድር ላይ፥ ሰውም በማይኖርበት ምድረ በዳ ይዘንም ዘንድ፥
26 በዚህም ማንም የማይኖርበትን ምድር፣ ሰውም የሌለበትን ምድረ በዳ የሚያጠጣ፣
26 እንዲሁም ማንም በሌለበት ምድር፥ ሰው በማይኖርበት ምድረ በዳ፥
እነዚህን በፈጠረ ጊዜ እንዲሁ ዐውቆ ቈጠራቸው። ለዝናም ሥርዐትን ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን አደረገ።
የዝናቡም ነጠብጣቦች በእርሱ ይቈጠራሉ። ዝናብም ከደመና ይንጠባጠባል፤
ይኸውም፥ ለተግሣጽ ወይም ለምድሩ ወይም በምሕረት ለሚያገኘው እንዲሆን ነው።
ለኀይለኛው ዝናብ መውረጃውን፥ ወይስ ለሚያንጐዳጕደው መብረቅ መንገድን ያዘጋጀ ማንነው?
በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ ከሰማይም በታች ውኃን ይልካል።
ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
በራሳችን ላይ ሰውን አስጫንህ፤ በእሳትና በውኃ መካከል አሳለፍኸን፥ ወደ ዕረፍትም አወጣኸን።
በላይ በሰማይ ውኆችን ይሰበስባል፤ ከምድርም ዳርቻ ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።
በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰጥና ሊያጠግብ ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።