Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 34:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ሰለ​ዚህ እና​ንተ አእ​ምሮ ያላ​ቸሁ ሰዎች ስሙኝ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዘንድ ትበ​ድሉ ዘንድ አት​ው​ደዱ። ሁሉን በሚ​ችል አም​ላክ ፊትም ጻድ​ቁን አታ​ው​ኩት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ስለዚህ፣ እናንተ አስተዋዮች ስሙኝ፤ ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ በደልንም መፈጸም ሁሉን ቻይ አምላክ ይራቅ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 “ስለዚህ የምታስተውሉ ሰዎች፥ ስሙኝ፥ ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር፥ በደልንም መፈጸም ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “አስተዋዮች የሆናችሁ ሰዎች አድምጡኝ! ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር፥ ስሕተትንም ማድረግ ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ስለዚህ እናንተ አእምሮ ያላችሁ ሰዎች፥ ስሙኝ፥ ክፋትን ያደርግ ዘንድ ከእግዚአብሔር፥ በደልንም ይሠራ ዘንድ ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ።

参见章节 复制




ኢዮብ 34:10
19 交叉引用  

አቤቱ ይህ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ ይህን ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ጻድ​ቃ​ንን ከኃ​ጥ​ኣን ጋር አታ​ጥፋ፤ ምድ​ርን ሁሉ የም​ት​ገዛ ይህን ፍርድ ታደ​ርግ ዘንድ ለአ​ንተ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም።”


የኀ​ያል አም​ላክ መን​ገድ ንጹሕ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ጽኑዕ ነው፤ በእ​ሳ​ትም የጋለ ነው፤ በእ​ር​ሱም ለሚ​ታ​መ​ኑት ጠባ​ቂ​ያ​ቸው ነው።


አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት በእ​ና​ንተ ላይ ይሁን፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በደ​ልና ለሰው ፊት ማድ​ላት፥ መማ​ለ​ጃም መው​ሰድ የለ​ምና ሁሉን ተጠ​ን​ቅ​ቃ​ችሁ አድ​ርጉ” አላ​ቸው።


በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ግፍ እን​ደ​ሚ​ሠራ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ህን? ወይስ ምድ​ርን የፈ​ጠረ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላክ ፍር​ድን ያጣ​ም​ማ​ልን?


የልብ ጥበ​በ​ኞች እን​ዲህ ይላ​ሉና፦ ጠቢብ ሰው ነገ​ሬን ይሰ​ማ​ኛል።


ሥራ​ው​ንስ የሚ​መ​ረ​ምር ማን ነው? ወይስ፦ ክፉ ሠር​ተ​ሃል የሚ​ለው ማን ነው?


በኀ​ይል ከእ​ርሱ ጋር እኩል የሚ​ሆን፥ እው​ነ​ት​ንም የሚ​ፈ​ርድ ሌላ አና​ገ​ኝም። እርሱ እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ታስ​ባ​ለ​ህን?


በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​መፅ ይፈ​ር​ዳ​ልን? ሁሉን የፈ​ጠረ አም​ላ​ክስ ጽድ​ቅን ያጣ​ም​ማ​ልን?


ከተግሣጽ የሚከላከል ራሱን ይጠላል። ተግሣጽን የሚወድድ ግን ራሱን ይወድዳል።


አመንዝራ ግን በአእምሮው ጉድለት፥ ነፍሱ የሚጠፋበትን ጥፋት ይሠራል።


አቤቱ! ከአ​ንተ ጋር በተ​ም​ዋ​ገ​ትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ጋር ስለ ፍርድ ልና​ገር። የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች መን​ገድ ስለ ምን ይቀ​ናል? በደ​ል​ንስ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላ​ቸ​ዋል?


እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፣ ክፋትን አያደርግም፣ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፣ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ላ​ልን? አያ​ደ​ላም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሥ​ራው እው​ነ​ተኛ ነው፤ መን​ገ​ዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የታ​መነ ነው፤ ክፋ​ትም የለ​በ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድ​ቅና ቸር ነው።


ማንም ሲፈተን “በእግዚአብሔር እፈተናለሁ፤” አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም።


跟着我们:

广告


广告