6 በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ቅንነቴን ያውቃል።
6 እግዚአብሔር በጽድቅ ሚዛን ይመዝነኝ፤ ነውር እንደሌለብኝም ይወቅ።
6 እግዚአብሔር በትክክለኛ ሚዛን ይመዝነኝ፤ በቅንነት መጽናቴንም ይወቅ።
መንገዴን ፈጽሞ ዐወቀ፥ እንደ ወርቅም ፈተነኝ
ኢዮብም በፊታቸው ራሱን ጻድቅ አድርጎ ነበርና እነዚያ ሦስቱ ወዳጆቹ ለኢዮብ ለመመለስ ዝም አሉ።
“ከእናንተ አንዱ መቅሠፍቴን ምነው በመዘነ ኖሮ! መከራዬንም በአንድነት ምነው በሚዛን ላይ ባኖረው ኖሮ!
ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና፤ ነገር ግን ቃሌ ሐሰትን ይመስላል።
እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የኃጥኣን መንገድ ግን ትጠፋለች።
እግዚአብሔር ያበራልኛል፥ ያድነኛልም፤ ምን ያስፈራኛል? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ ምን ያስደነግጠኛል?
የእግዚአብሔር ፍርድ እንደ ሚዛን ውልብልቢት ነው፤ ሥራውም የከረጢት ደንጊያ ነው።
ሰው ሁሉ ለራሱ ጻድቅ መስሎ ይታያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያቀናል።
የጻድቃን መንገድ የቀና ትሆናለች፤ የቅኖችም መንገድ ትጠረጋለች።
በአባይ ሚዛንና በከረጢት ባለ በተንኰል መመዘኛ ንጹሕ እሆናለሁን?
የዚያን ጊዜም ‘ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ አመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ’ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።
ሆኖም “ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል፤” ደግሞም “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዐመፅ ይራቅ፤” የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል።
“እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ነው፤ እርሱ ያውቃል። እስራኤልም ያውቀዋል። በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ለበደልና ለመካድ ከሆነ ዛሬ አያድነን፤
አትመኩ፤ የኵራት ነገሮችንም አትናገሩ፤ ፅኑዕ ነገርም ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ዙፋኑን ያዘጋጃል።