Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 22:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን ታገ​ኛ​ለህ። ወደ ሰማ​ይም በደ​ስታ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚያ ጊዜ በሁሉን ቻይ አምላክ ደስ ይልሃል፤ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታቀናለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፤ በእርሱም ተማምነህ ትኖራለህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።

参见章节 复制




ኢዮብ 22:26
16 交叉引用  

በዚ​ያን ጊዜ ፊትህ በን​ጹሕ ውኃ እንደ ታጠበ ያበ​ራል፥ መተ​ዳ​ደ​ፍ​ህ​ንም ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ፥ አት​ፈ​ራ​ምም።


ጸሎ​ትህ እንደ አጥ​ቢያ ኮከብ ይሆ​ናል። ሕይ​ወ​ት​ህም እንደ ቀትር ብር​ሃን ያበ​ራል።


ሁሉን የሚ​ችል አም​ላ​ክም ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ይረ​ዳ​ሃል። ንጽ​ሕ​ና​ንም በእ​ሳት እንደ ተፈ​ተነ ብር አድ​ርጎ ይመ​ል​ስ​ል​ሃል።


በእ​ርሱ ዘን​ድስ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን ያገ​ኛ​ልን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ በጠራ ጊዜ ይመ​ል​ስ​ለ​ታ​ልን?


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ል​ያል፥ ጸሎ​ቱም ተቀ​ባ​ይ​ነ​ትን ያገ​ኛል። በደ​ስ​ተ​ኛም ፊት እያ​መ​ሰ​ገነ ይገ​ባል፥ ለሰ​ውም ጽድ​ቁን ይመ​ል​ስ​ለ​ታል።


ሰው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጕብ​ኝት ሲኖ​ረው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ጐ​በ​ኘ​ውም አት​በል።


ሰላ​ምን ከሚ​ጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገ​ሠች።


አፋ​ቸው ከንቱ ነገ​ርን ከሚ​ና​ገር፥ ቀኛ​ቸ​ውም የዐ​መፃ ቀኝ ከሆነ አስ​ጥ​ለኝ።


አቤቱ፥ እኔ በየ​ዋ​ህ​ነቴ እኖ​ራ​ለ​ሁና ፍረ​ድ​ልኝ፤ እን​ዳ​ል​ደ​ክም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አመ​ንሁ።


ኀጢ​አቴ ከራሴ ጠጕር በዝ​ቷ​ልና፥ እንደ ከባድ ሸክ​ምም በላዬ ከብ​ዶ​አ​ልና።


የሚ​ያ​ው​ቁ​ኝን ረዓ​ብ​ንና ባቢ​ሎ​ንን አስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነሆ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን፥ ጢሮ​ስም የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ሕዝብ፥ እነ​ዚህ በዚያ ተወ​ለዱ።


በዱር እን​ዳለ እን​ኮይ፥ እን​ዲሁ ውዴ በወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ነው። ከጥ​ላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀ​መ​ጥሁ፥ ፍሬ​ውም ለጕ​ሮ​ሮዬ ጣፋጭ ነው።


በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትታ​መ​ና​ለህ፤ በም​ድ​ርም በረ​ከት ላይ ያወ​ጣ​ሃል፤ የአ​ባ​ትህ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ርስት ይመ​ግ​ብ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ደ​ዚህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


በል​ቡ​ናዬ ውስጥ ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መል​ካም ነው።


ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።


跟着我们:

广告


广告