Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 21:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በነ​ፋ​ስም ፊት እንደ ገለባ፥ አውሎ ነፋ​ስም እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ይሆ​ናሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በነፋስ ፊት እንዳለ ገለባ፣ በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ዕብቅ የሆኑት ስንት ጊዜ ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በነፋስ ፊት እንደ ገለባ፥ ዐውሎ ነፋስም እንደሚወስደው ትቢያ የሆኑት ስንት ጊዜ ነው?”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንደ ገለባ በነፋስ የተወሰዱበት፥ እንደ ትቢያም በዐውሎ ነፋስ የተጠረጉበት ጊዜ አለን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በነፋስ ፊት እንደ ገለባ፥ ዐውሎ ነፋስም እንደሚወስደው ትቢያ የሆኑ ስንት ጊዜ ነው?

参见章节 复制




ኢዮብ 21:18
20 交叉引用  

በነ​ፋስ እንደ ረገፈ ቅጠል ታፍ​ሰ​ኛ​ለ​ህን? ወይስ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ዕብቅ ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለ​ህን?


ጊዜ​ያ​ቸው ሳይ​ደ​ርስ ተነ​ጠቁ፤ መሠ​ረ​ታ​ቸ​ውም እንደ ፈሳሽ ውኃ ፈሰሰ።


የሚ​ያ​ቃ​ጥል ነፋስ ያነ​ሣ​ዋል፥ እር​ሱም ያል​ፋል፤ ከቦ​ታ​ውም ይጠ​ር​ገ​ዋል።


ኃጥ​ኣን እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም፥ እን​ዲህ አይ​ደ​ሉም። ነገር ግን ነፋስ ከገጸ ምድር ጠርጎ እን​ደ​ሚ​ወ​ስ​ደው ትቢያ ናቸው።


አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ በሰ​ማይ ነው፥ እው​ነ​ት​ህም እስከ ደመ​ናት ትደ​ር​ሳ​ለች።


በክ​ብ​ር​ህም ብዛት ጠላ​ቶ​ች​ህን አጠ​ፋህ፤ ቍጣ​ህን ሰደ​ድህ፤ እንደ ገለ​ባም በላ​ቸው።


ኃጥእ እንደ ዐውሎ ነፋስ ኅልፈት ይጠፋል፤ ጻድቅ ግን ተሰውሮ ለዘለዓለም ይድናል።


ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏ​ፏቴ ውስጥ በኀ​ይል እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮ​ኻሉ፤ ያጠ​ፉ​ታ​ልም፤ እነ​ር​ሱም ከሩቅ ይወ​ር​ዳሉ፤ በተ​ራ​ራም ላይ እን​ዳለ እብቅ፥ በነ​ፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እን​ደ​ሚ​ያ​ዞ​ረው እንደ መን​ኰ​ራ​ኵር ትቢ​ያም ይበ​ተ​ናሉ።


ነገር ግን የኃ​ጥ​አን ብል​ጽ​ግና እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጠ​ላ​ቶ​ች​ሽም ብዛት ነፋስ እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ጣው ገለባ ይሆ​ናል።


በእ​ር​ሱም ላይ ዛፉ​ንና ሣሩን፥ የማ​ይ​ቈ​ጠር ሌላ​ው​ንም ብዙ ፍጥ​ረት የፈ​ጠረ እርሱ ነው። ነፋ​ስም በነ​ፈ​ሰ​ባ​ቸው ጊዜ ይደ​ር​ቃሉ፤ ዐውሎ ነፋ​ስም እንደ ገለባ ይጠ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።


ስለ​ዚህ ገለባ በእ​ሳት ፍም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል፥ በነ​በ​ል​ባ​ልም እን​ደ​ሚ​በላ፥ እን​ዲሁ የእ​ነ​ርሱ ሥር የበ​ሰ​በሰ ይሆ​ናል፤ አበ​ባ​ቸ​ውም እንደ ትቢያ ይበ​ን​ናል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ጥለ​ዋ​ልና፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል አቃ​ል​ለ​ዋ​ልና።


ነፋስ በም​ድረ በዳ እን​ደ​ሚ​በ​ት​ነው እብቅ እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም እንደ ማለዳ ደመና፥ በጥ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል፥ በዐ​ውሎ ነፋ​ስም ከዐ​ው​ድማ እን​ደ​ሚ​በ​ተን እብቅ፥ ከም​ድ​ጃም እን​ደ​ሚ​ወጣ ጢስ ይሆ​ናሉ።


እርስ በእርሳቸው እንደ ተመሰቃቀለ እሾህ ቢሆኑ፥ በመጠጣቸውም ቢሰክሩ እንደ ደረቅ ገለባ ፈጽመው ይጠፋሉ።


ቆመ፥ ምድርንም አወካት፣ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፣ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፣ መንገዱ ከዘላለም ነው።


መንሹም በእጁ ነው፤ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


በዚህ መሠ​ረት ላይ በወ​ር​ቅና በብር፥ በከ​በረ ድን​ጋ​ይና በእ​ን​ጨት፥ በሣ​ርና በአ​ገዳ የሚ​ያ​ንጽ ቢኖ​ርም፥


跟着我们:

广告


广告