Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 2:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሦስ​ቱም የኢ​ዮብ ወዳ​ጆች ይህን የደ​ረ​ሰ​በ​ትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰም​ተው ከየ​ሀ​ገ​ራ​ቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነ​ር​ሱም ቴማ​ና​ዊው ንጉሥ ኤል​ፋዝ፥ አው​ኬ​ና​ዊው መስ​ፍን በል​ዳ​ዶስ፥ አሜ​ና​ዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነ​ር​ሱም ሊጐ​በ​ኙ​ትና ሊያ​ጽ​ና​ኑት በአ​ን​ድ​ነት ወደ እርሱ መጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዳዶስ፣ ናዕማታዊውም ሶፋር በኢዮብ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ሄደው ሊያስተዛዝኑትና ሊያጽናኑት በመስማማት ከየመኖሪያቸው በአንድነት መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው ቢልዳድ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ፥ የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድና የናዕማ አገር ሰው የሆነው ጾፋር፥ እነዚህ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ነበሩ። እነርሱም በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሥቃይ በሰሙ ጊዜ ሐዘናቸውን ሊገልጹለትና ሊያጽናኑት ከየአገራቸው ተጠራርተው በአንድነት ወደ ኢዮብ መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየአገራቸው መጡ፥ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊያዝኑለትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ ለመምጣት ተስማሙ።

参见章节 复制




ኢዮብ 2:11
34 交叉引用  

እር​ስ​ዋም ዘን​በ​ሪን፥ ዮቃ​ጤ​ንን፥ ሜዳ​ንን፥ ዮብ​ቅን፥ ምድ​ያ​ም​ንና ሴሂን ወለ​ደ​ች​ለት።


የዔ​ሳው ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኤሞር፥ ሳፍር፥ ጎቶን፥ ቄኔዝ።


የዔ​ሳው ልጆች መሳ​ፍ​ንት እነ​ዚህ ናቸው፤ የዔ​ሳው የበ​ኵር ልጅ የኤ​ል​ፋዝ ልጆች፤ ቴማን መስ​ፍን፥ ኦሜር መስ​ፍን፥ ሳፍር መስ​ፍን፥ ቄኔዝ መስ​ፍን፥


ኢዮ​ባ​ብም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፈንታ የቴ​ማ​ኒው ሀገር ሑሳም ነገሠ።


ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።


የአ​ብ​ር​ሃም ዕቅ​ብት ኬጡራ የወ​ለ​ደ​ች​ለት ልጆች፤ ዘም​ራን፥ ዮቅ​ሳን፥ ሜዳም፥ ምድ​ያን፥ ዮሳ​ብቅ፥ ስዌሕ፥ የዮ​ቅ​ሳ​ንም ልጆች፤ ሳባ፥ ዳዳን።


ኢዮ​ባ​ብም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የቴ​ማን ሀገር ሰው አሶም ነገሠ፤


አባ​ታ​ቸው ኤፍ​ሬ​ምም ብዙ ቀን አለ​ቀሰ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም ሊያ​ጽ​ና​ኑት መጡ።


አሜ​ና​ዊው ሶፋር መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦


እና​ንተ ግን የዐ​መፅ ባለ መድ​ኀ​ኒ​ቶች፥ ሁላ​ች​ሁም የክ​ፋት ፈዋ​ሾች ናችሁ።


ቴማ​ና​ዊ​ውም ኤል​ፋዝ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦


“እን​ደ​ዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰማሁ፤ እና​ንተ ሁላ​ችሁ የም​ታ​ደ​ክሙ አጽ​ና​ኞች ናችሁ።


“አሁ​ንም፥ እነሆ፥ ምስ​ክሬ በሰ​ማይ አለ፤ የሚ​ያ​ው​ቅ​ል​ኝም በአ​ር​ያም ነው።


አው​ኬ​ና​ዊው በል​ዳ​ዶስ መለሰ እን​ዲ​ህም አለ፦


ያዩኝ ሁሉ ተጸ​የ​ፉኝ፤ እኔ የም​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ውም በላዬ ተነሡ።


እና​ንተ ወዳ​ጆቼ ሆይ፤ ማሩኝ፤ ማሩኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ዳስ​ሳ​ኛ​ለ​ችና።


ቴማ​ና​ዊ​ውም ኤል​ፋዝ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦


ወን​ድ​ሞ​ቹና እኅ​ቶቹ ቀድ​ሞም ያው​ቁት የነ​በ​ሩት ሁሉ የሆ​ነ​ውን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ወደ እርሱ መጡ፥ በቤ​ቱም ከእ​ርሱ ጋር እን​ጀራ በሉ፥ ጠጡም፤ አጽ​ና​ኑ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባመ​ጣ​በት ክፉ ነገር ሁሉ አደ​ነቁ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም ጥማድ በሬ፥ አራት ድራ​ህማ የሚ​መ​ዝን ወር​ቅና ብር ሰጡት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ቃል ለኢ​ዮብ ከተ​ና​ገረ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቴማ​ና​ዊ​ውን ኤል​ፋ​ዝን እን​ዲህ አለው፥ “እንደ ባሪ​ያዬ እንደ ኢዮብ አን​ዲት ቅን ነገ​ርን በፊቴ አል​ተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁ​ምና አን​ተና ሁለቱ ባል​ን​ጀ​ሮ​ችህ በድ​ላ​ች​ኋል።


ቴማ​ና​ዊ​ውም ኤል​ፋዝ፥ አው​ኬ​ና​ዊው በል​ዳ​ዶ​ስና፥ አሜ​ና​ዊው ሶፋር ሄደው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ፤ ስለ ኢዮ​ብም ሲል ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር አላ​ቸው።


ምሕ​ረቱ ቸል አለኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ጐ​በ​ኘ​ኝም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ተ​ኝም።


የቴ​ማ​ና​ው​ያ​ንን መን​ገ​ዶች፥ የሳ​ባ​ው​ያ​ንን ክፋ​ትና ቸል​ተ​ኝ​ነት ተመ​ል​ከቱ።


አው​ኬ​ና​ዊው በል​ዳ​ዶስ መለሰ፥ እን​ዲ​ህም አለ፦


ሁልጊዜ ወዳጅ ይኑርህ፥ ወንድሞች በመከራ ጊዜ ጠቃሚዎች ይሆናሉ፥ ስለዚህ ይወለዳሉና።


አሁ​ንም እነ​ዚህ ሁለቱ ይጠ​ብ​ቁ​ሻል፤ ማን ያስ​ተ​ዛ​ዝ​ን​ሻል? እነ​ር​ሱም ጥፋ​ትና ውድ​ቀት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እን​ግ​ዲህ የሚ​ያ​ጽ​ና​ናሽ ማን ነው?


ስለ ኤዶ​ም​ያስ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴ​ማን ጥበብ የለ​ምን? ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችስ ምክር ጠፍ​ቶ​አ​ልን? ጥበ​ባ​ቸ​ውስ አል​ቆ​አ​ልን?


ከዔ​ሳው ተራራ ሰዎች ሁሉ ይጠፉ ዘንድ የቴ​ማን ሰል​ፈ​ኞ​ችህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


ከአ​ይ​ሁ​ድም ስለ ወን​ድ​ማ​ቸው ሊያ​ጽ​ና​ኑ​አ​ቸው ወደ ማር​ያ​ምና ወደ ማርታ የሄዱ ብዙ​ዎች ነበሩ።


ደስ ከሚ​ለው ጋር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከሚ​ያ​ለ​ቅ​ሰው ጋርም አል​ቅሱ።


አንዱ የአ​ካል ክፍል ቢታ​መም ከእ​ርሱ ጋር የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ይታ​መ​ማሉ፤ አንዱ የአ​ካል ክፍል ደስ ቢለ​ውም የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ራ​ች​ኋ​ቸው እንደ ታሰ​ራ​ችሁ ሆና​ችሁ እስ​ረ​ኞ​ችን ዐስቡ፤ መከራ የጸ​ና​ባ​ቸ​ው​ንም በሥ​ጋ​ችሁ ከእ​ነሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ችሁ ሆና​ችሁ ዐስቡ።


ጌዶር፥ በጋ​ድ​ያል፥ ኖማን፥ መቄ​ዶም፥ ዐሥራ ስድ​ስት ከተ​ሞ​ችና መን​ደ​ሮ​ቻ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告