Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 18:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በሌ​ሊት በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ለእ​ርሱ የማ​ይ​ሆ​ነው ይኖ​ራል፤ የእ​ር​ሱም መል​ካም ነገር በዲን ይበ​ተ​ናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ድንኳኑ በእሳት ይያያዛል፤ በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በድንኳኑ ውስጥ ለእርሱ የማይሆነው ይኖራል፥ በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በቤቱ ውስጥ ምንም ነገር አይቀርለትም፤ በመኖሪያውም ውስጥ ዲን ይበተናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በድንኳኑ ውስጥ ለእርሱ የማይሆነው ይኖራል፥ በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።

参见章节 复制




ኢዮብ 18:15
16 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ዶ​ምና በገ​ሞራ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን አዘ​ነበ፤


ለኃ​ጥ​ኣን ሁሉ ሞት ምስ​ክ​ራ​ቸው ነው፥ እሳት የጉቦ ተቀ​ባ​ዮ​ችን ቤት ይበ​ላል።


በም​ድር ላይ እንደ ተፈ​ተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።


ቤቱን በዐ​መፅ፥ አዳ​ራ​ሹ​ንም ያለ እው​ነት ለሚ​ሠራ፥ ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም እን​ዲ​ያው በከ​ንቱ ለሚ​ያ​ሠራ፥ ዋጋ​ው​ንም ለማ​ይ​ሰ​ጠው ወዮ​ለት!


ሰዶ​ምና ገሞራ፥ በእ​ነ​ር​ሱም አጠ​ገብ የነ​በ​ሩት ከተ​ሞች እንደ ተገ​ለ​በጡ፥ ይላል ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዲሁ በዚያ ሰው አይ​ቀ​መ​ጥም፤ የሰው ልጅም አይ​ኖ​ር​ባ​ትም።


እኔ አስወጣዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ወደ ሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፣ በቤቱም ውስጥ ይኖራል፥ እርሱንም፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።


ሎጥ ከሰ​ዶም በወ​ጣ​በት ቀን ግን ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን ዘነመ፤ ሁሉ​ንም አጠፋ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ር​ህን ዝናብ ጭጋግ ያደ​ር​ጋል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ ከሰ​ማይ አፈር ይወ​ር​ድ​ብ​ሃል።


ምድ​ርም በሁ​ለ​ን​ተ​ናዋ ዲንና ጨው፥ መቃ​ጠ​ልም እንደ ሆነ​ባት፥ እን​ዳ​ይ​ዘ​ራ​ባ​ትም፥ እን​ዳ​ታ​በ​ቅ​ልም፥ ማና​ቸ​ውም ሣርና ልም​ላ​ሜም እን​ዳ​ይ​ወ​ጣ​ባት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣ​ውና በመ​ዓቱ እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው እንደ ሰዶ​ምና ገሞራ፥ እንደ አዳ​ማና እንደ ሲባዮ እንደ ሆነች ባዩ ጊዜ፥


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”


跟着我们:

广告


广告