Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 14:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “በመ​ቃ​ብር ውስጥ ምነው በጠ​በ​ቅ​ኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስ​ኪ​በ​ር​ድም ድረስ በሸ​ሸ​ግ​ኸኝ ኖሮ! እስ​ከ​ም​ታ​ስ​በ​ኝም ምነው ቀጠሮ በሰ​ጠ​ኸኝ ኖሮ!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “ምነው መቃብር ውስጥ በሰወርኸኝ! ቍጣህም እስከሚያልፍ በሸሸግኸኝ! ምነው ቀጠሮ ሰጥተህ፣ ከዚያ በኋላ ባስታወስኸኝ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቁጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “ምነው፥ በሙታን ዓለም ብትሰውረኝ! ቊጣህም እስከሚያልፍ ብትሸሽገኝ! የቀጠሮም ቀን ወስነህ ብታስበኝ!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!

参见章节 复制




ኢዮብ 14:13
13 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኖኅን፥ በመ​ር​ከ​ብም ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ረ​ውን አራ​ዊ​ቱን ሁሉ፥ እን​ስ​ሳ​ው​ንም ሁሉ፥ አዕ​ዋ​ፍ​ንም ሁሉ፥ የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ሰ​ው​ንም ሁሉ ዐሰበ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በም​ድር ላይ ነፋ​ስን አመጣ፤ ውኃ​ውም ጐደለ፤


ሰው የሕ​ይ​ወ​ቱን ዘመን ፈጽሞ ከሞተ በኋላ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖር ቢሆን ዳግ​መኛ እስ​ክ​ወ​ለድ ድረስ፥ በት​ዕ​ግ​ሥት በተ​ጠ​ባ​በ​ቅሁ ነበር።


ደመና ከሰ​ማይ ተበ​ትኖ እን​ደ​ሚ​ጠፋ፥ እን​ዲሁ ወደ መቃ​ብር የሚ​ወ​ርድ ሰው ዳግ​መኛ አይ​ወ​ጣም።


ውኃ በሌ​ለ​በት ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በዙ፤ የሚ​ኖ​ሩ​በ​ት​ንም ከተማ መን​ገድ አላ​ገ​ኙም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ይመታ ዘንድ ያል​ፋ​ልና፤ ደሙ​ንም በጉ​በ​ኑና በሁ​ለቱ መቃ​ኖች ላይ በአየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሩን ያል​ፋል፤ አጥ​ፊ​ውም ይመ​ታ​ችሁ ዘንድ ወደ ቤታ​ችሁ እን​ዲ​ገባ አይ​ተ​ወ​ውም።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ለህ፥ “አቤቱ፥ ተቈ​ጥ​ተ​ኸ​ኛ​ልና፥ ቍጣ​ህ​ንም ከእኔ መል​ሰ​ሃ​ልና፥ ዳግ​መ​ኛም ይቅር ብለ​ኸ​ኛ​ልና አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


“ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም፥ “አቤቱ፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በመ​ጣህ ጊዜ ዐስ​በኝ” አለው።


እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አብ በገዛ ሥል​ጣኑ የወ​ሰ​ነ​ውን ቀኑ​ንና ዘመ​ኑን ልታ​ውቁ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ች​ሁም።


በመ​ረ​ጠው ሰው እጅ በዓ​ለም በእ​ው​ነት የሚ​ፈ​ር​ድ​ባ​ትን ቀን ወስ​ኖ​አ​ልና፤ እር​ሱን ከሙ​ታን ለይቶ በማ​ስ​ነ​ሣ​ቱም ብዙ​ዎ​ችን ወደ ሃይ​ማ​ኖት መል​ሶ​አ​ልና።”


跟着我们:

广告


广告