14 በእጆችህ በደል ቢኖር ካንተ አርቀው፤ በልብህም ኀጢአት አይኑር፤
14 በእጅህ ያለውን ኀጢአት ብታርቅ፣ ክፋትም በድንኳንህ እንዳይኖር ብታደርግ፣
14 ኃጢአትን ከእጅህ ብታርቅ፥ ክፉ ነገርም በቤትህ እንዲገኝ ባታደርግ፥
በእውነት ያመጣህልኝ አይደለም፤ አግባብስ በእውነት ታመጣልኝ ዘንድ ነበር። በደልህ፤ እንግዲህ ዝም በል፤ የወንድምህ መመለሻው ወደ አንተ ነው፤ አንተም ትሰለጥንበታለህ።”
እግዚአብሔርም፥ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።
ብትመለስ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ራስህን ብታዋርድ፥ ኀጢአትንም ከልብህ ብታርቅ፥
“ክፋትህስ የበዛ አይደለምን? ኀጢአትህስ ቍጥር የሌለው አይደለምን?
እኔ ራሴ አያለሁ፥ ኀጢአትንም ሠርቼ እንደ ሆነ፥ ሐሰትንም ተናግሬ እንደ ሆነ፥ ደግሜ እንዳልሠራ አንተ አሳየኝ።
እባክህ አስብ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን ነው? ከጻድቃንስ የተደመሰሰ ማን ነው?
ንጹሕና ጻድቅ ብትሆን፥ ልመናህን ፈጥኖ ይሰማሃል፥ የጽድቅህንም ብድራት ፈጽሞ ይሰጥሃል።
በመከራዬ ቀን ፊትህን ከእኔ አትመልስ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ።
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ! ልባችሁን አጥሩ።
ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ “በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና ምስሎቻቸውን ከመካከላችሁ አርቁ፤ ልባችሁንም ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፤ እርሱንም ብቻ አምልኩ፤ እርሱም ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል” ብሎ ተናገራቸው።